የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp21 ቁጥር 2 ገጽ 7-9
  • የዓለም ፍጻሜ የሚሆነው መቼ ነው? ኢየሱስ ምን ብሏል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የዓለም ፍጻሜ የሚሆነው መቼ ነው? ኢየሱስ ምን ብሏል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ የዓለም ፍጻሜን በተመለከተ የተናገራቸውን ሁለት ሐሳቦች እስቲ እንመልከት፦
  • የዓለም ፍጻሜ መቅረቡን የሚጠቁመው ምልክት
  • ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’
  • ምድር ገነት የምትሆንበት ጊዜ ቀርቧል!
  • የመጨረሻውን ዘመን በተመለከተ የሚነሱ አራት ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • የምንኖረው “በመጨረሻው ዘመን” ውስጥ ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • የአምላክ ዓላማ በቅርቡ ይፈጸማል
    የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?
  • የዓለም መጨረሻ ቀርቧል?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
wp21 ቁጥር 2 ገጽ 7-9
ኢየሱስ፣ የመጨረሻዎቹ ቀናት ምልክት ምን እንደሆነ ለሐዋርያቱ ሲያብራራ።

የዓለም ፍጻሜ የሚሆነው መቼ ነው? ኢየሱስ ምን ብሏል?

ቀደም ባለው ርዕስ ላይ እንደተመለከትነው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዓለም ፍጻሜ ሲናገር ምድር ወይም የሰው ዘር በአጠቃላይ እንደሚጠፉ መናገሩ አይደለም። ከዚህ ይልቅ፣ ይህ ብልሹ ሥርዓትና የዚህ ሥርዓት ደጋፊዎች ስለሚጠፉበት ጊዜ መናገሩ ነው። ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ፣ ይህ ክፉ ሥርዓት መቼ እንደሚጠፋ ይናገራል?

ኢየሱስ የዓለም ፍጻሜን በተመለከተ የተናገራቸውን ሁለት ሐሳቦች እስቲ እንመልከት፦

“እንግዲህ ቀኑንም ሆነ ሰዓቱን ስለማታውቁ ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ።”—ማቴዎስ 25:13

“ስለዚህ የተወሰነው ጊዜ መቼ እንደሆነ ስለማታውቁ ምንጊዜም በንቃት ተከታተሉ፤ ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ።”—ማርቆስ 13:33

በመሆኑም በዚህ ሥርዓት ላይ ጥፋት የሚመጣበትን ትክክለኛ ጊዜ የሚያውቅ ሰው የለም። ይሁንና ፍጻሜው የሚሆነው አምላክ ‘በወሰነው ጊዜ’ ላይ ነው፤ አምላክ ጥፋቱ የሚመጣበትን “ቀንና ሰዓት” አስቀድሞ ወስኗል። (ማቴዎስ 24:36) ታዲያ ያ ጊዜ መቅረቡን የምናውቅበት ምንም መንገድ የለም ማለት ነው? እንደዛ ማለት አይደለም። ኢየሱስ፣ የዓለም ፍጻሜ መቅረቡን የሚጠቁሙ ክንውኖችን ለደቀ መዛሙርቱ ነግሯቸዋል።

የዓለም ፍጻሜ መቅረቡን የሚጠቁመው ምልክት

“የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ” መቅረቡን የሚጠቁሙት ክስተቶች እነዚህ ናቸው። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳልና፤ በተለያየ ስፍራ የምግብ እጥረትና የምድር ነውጥ ይከሰታል።” (ማቴዎስ 24:3, 7) በተጨማሪም “ቸነፈር” ማለትም ተላላፊ በሽታዎች እንደሚከሰቱ ተናግሯል። (ሉቃስ 21:11) ኢየሱስ በትንቢት የተናገራቸው እነዚህ ክስተቶች ሲፈጸሙ እያየህ ነው?

አውዳሚ ጦርነቶች፣ ረሃብ፣ የምድር ነውጥ እንዲሁም አስከፊ በሽታዎች በዛሬው ጊዜ ብዙ መከራ እያስከተሉ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ በ2004 በሕንድ ውቅያኖስ ላይ የተከሰተው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ የቀሰቀሰው ሱናሚ ለ225,000 ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ 6.9 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። ኢየሱስ እንዲህ ያሉት ክስተቶች የዚህ ሥርዓት ፍጻሜ መቅረቡን እንደሚጠቁሙ ተናግሯል።

‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’

መጽሐፍ ቅዱስ፣ የዓለም ፍጻሜ ከመከሰቱ ጥቂት ቀደም ብሎ ያለውን ጊዜ ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ ብሎ ይጠራዋል። (2 ጴጥሮስ 3:3, 4) ሁለተኛ ጢሞቴዎስ 3:1-5 በእነዚህ የመጨረሻዎቹ ቀናት ከፍተኛ የሥነ ምግባር ውድቀት እንደሚከሰት ይናገራል። (“የዓለም ፍጻሜ ከመከሰቱ ጥቂት ቀደም ብሎ” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።) ሰዎች ራስ ወዳድ፣ ስግብግብና ጨካኝ እየሆኑ እንደመጡ አስተውለሃል? እነዚህ ነገሮችም የዓለም ፍጻሜ በጣም እንደቀረበ ማስረጃ ይሆናሉ።

ታዲያ የመጨረሻዎቹ ቀናት የሚቆዩት እስከ መቼ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ‘ለጥቂት ጊዜ’ ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ አምላክ “ምድርን እያጠፉ ያሉትን” ያጠፋል።—ራእይ 11:15-18፤ 12:12

ጦርነት

ውጊያ ላይ ያሉ ወታደሮች ምሽጋቸው ውስጥ ሆነው ሲተኩሱ።
  • ከ2007 እስከ 2017 ባለው ጊዜ ውስጥ በጦርነትና በሽብርተኝነት ምክንያት የሞቱት ሰዎች ብዛት ከእጥፍ በላይ ጨምሯል

በሽታ

አንድ የታመመ ሰው ሆስፒታል ውስጥ አልጋ ላይ ተኝቶ።
  • ገዳይ ከሆኑት መካከል የመጀመሪያውን ቦታ የሚይዙት የልብ በሽታ፣ ስትሮክ፣ የሳንባ በሽታ፣ በጨቅላ ሕጻናት ላይ የሚያጋጥሙ እክሎች፣ የተቅማጥ በሽታዎች፣ ካንሰርና ሳንባ ነቀርሳ ናቸው

ረሃብ

በረሃብ የተጠቃች አንዲት ሕፃን ጎድጓዳ ሳህን ይዛ።
  • በ2021 ከዓለም ሕዝብ 9.8 በመቶው በረሃብ ተጠቅቷል፤ ከአምስት ዓመት በታች ካሉ ሕፃናት መካከል ከሦስቱ አንዱ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት የተነሳ ቀንጭሯል

ዓለም አቀፍ ስብከት

የይሖዋ ምሥክሮች ከጽሑፍ መደርደሪያ ጋሪ አጠገብ ቆመው፤ አንድ ሰው እያነጋገሩ ነው።
  • ከ8.6 ሚሊዮን የሚበልጡ የሠለጠኑ ሰባኪዎች (የይሖዋ ምሥክሮች) በ240 አገሮች ውስጥ ከ1,000 በሚበልጡ ቋንቋዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን እያሰራጩ ነው

ምድር ገነት የምትሆንበት ጊዜ ቀርቧል!

አምላክ ይህን ክፉ ሥርዓት የሚያጠፋበትን ቀንና ሰዓት አስቀድሞ ወስኗል። (ማቴዎስ 24:36) ደስ የሚለው ግን፣ አምላክ ‘ማንም እንዲጠፋ አይፈልግም።’ (2 ጴጥሮስ 3:9) የሰው ልጆች የእሱን መመሪያዎች ታዝዘው አካሄዳቸውን እንዲያስተካክሉ አጋጣሚ ሰጥቷቸዋል። ይህን ያደረገው ለምንድን ነው? ምክንያቱም በዚህ ዓለም ላይ ከሚመጣው ጥፋት ተርፈን እሱ ባዘጋጀው አዲስ ዓለም ውስጥ እንድንኖር ስለሚፈልግ ነው፤ በዚያን ጊዜ ምድር ገነት ትሆናለች።

አምላክ ዓለም አቀፍ የትምህርት መርሃ ግብር አዘጋጅቷል፤ ይህን ያደረገው ሰዎች በእሱ መንግሥት በሚተዳደረው ዓለም ውስጥ ለመኖር ብቁ እንዲሆኑ ለመርዳት ነው። ኢየሱስ፣ የአምላክ መንግሥት ምሥራች “በመላው ምድር” እንደሚሰበክ ተናግሯል። (ማቴዎስ 24:14) በዓለም ዙሪያ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች፣ የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ለሰዎች በመስበክና በማስተማር በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዓታት አሳልፈዋል። ኢየሱስ፣ መጨረሻው ከመምጣቱ በፊት ይህ የስብከት ዘመቻ በመላው ምድር እንደሚካሄድ ተናግሯል።

የሰው አገዛዝ የሚያከትምበት ጊዜ በጣም ቀርቧል። ደስ የሚለው ነገር፣ በዓለም ላይ ከሚመጣው ጥፋት ተርፈህ አምላክ ቃል በገባልን ገነት ውስጥ መኖር ትችላለህ። በዚህ አዲስ ዓለም ውስጥ ለመኖር ምን ማድረግ እንደሚጠበቅብህ በቀጣዩ ርዕስ ላይ ይብራራል።

የዓለም ፍጻሜ ከመከሰቱ ጥቂት ቀደም ብሎ

“በመጨረሻዎቹ ቀናት ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን እንደሚመጣ ይህን እወቅ። ምክንያቱም ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፣ ገንዘብ የሚወዱ፣ ጉረኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ታማኝ ያልሆኑ፣ ተፈጥሯዊ ፍቅር የሌላቸው፣ ለመስማማት ፈቃደኞች ያልሆኑ፣ ስም አጥፊዎች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ ጥሩ ነገር የማይወዱ፣ ከዳተኞች፣ ግትሮች፣ በኩራት የተወጠሩ፣ ከአምላክ ይልቅ ሥጋዊ ደስታን የሚወዱ ይሆናሉ፤ ለአምላክ ያደሩ መስለው ይታያሉ፤ በሥራቸው ግን ኃይሉን ይክዳሉ።”—2 ጢሞቴዎስ 3:1-5

ኢየሱስ ስለ “መጨረሻዎቹ ቀናት” የተናገረው ትንቢት ተስፋ ይሰጠናል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ