የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp23 ቁጥር 1 ገጽ 14-15
  • ከአእምሮ ጤንነት መቃወስ ጋር የሚታገሉ ሰዎችን መርዳት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከአእምሮ ጤንነት መቃወስ ጋር የሚታገሉ ሰዎችን መርዳት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2023
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምን ማለት ነው?
  • ይህ ጥቅስ የሚረዳን እንዴት ነው?
  • የምትሰጠው እርዳታ ለውጥ ያመጣል
  • የታመመ ወዳጃችሁን መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • የጓደኛዬን ስህተት መናገር ይኖርብኛል?
    ንቁ!—2008
  • ድንገተኛ የጤና እክል ሲያጋጥም
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • እውነተኛ ጓደኞቼ እነማን ናቸው?
    ንቁ!—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2023
wp23 ቁጥር 1 ገጽ 14-15
አንድ ሰው በጭንቀት የተዋጠች ሚስቱን በርኅራኄ ሲያዳምጣት።

ከአእምሮ ጤንነት መቃወስ ጋር የሚታገሉ ሰዎችን መርዳት

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው፤ ደግሞም ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም ነው።”—ምሳሌ 17:17

ምን ማለት ነው?

አንድ ጓደኛችን የአእምሮ ሕመም ሲይዘው ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ ሊገባን ይችላል። ሆኖም ጓደኛችን ያጋጠመውን አስጨናቂ የአእምሮ ሕመም እንዲቋቋም በመርዳት አሳቢነታችንን ልናሳየው እንችላለን። ታዲያ ልንረዳው የምንችለው እንዴት ነው?

ይህ ጥቅስ የሚረዳን እንዴት ነው?

“ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ . . . መሆን አለበት።”—ያዕቆብ 1:19

ጓደኛህን መርዳት ከምትችልባቸው ወሳኝ መንገዶች አንዱ ማውራት ሲፈልግ ማዳመጥ ነው። ለሚናገረው ነገር ሁሉ ምላሽ መስጠት እንዳለብህ አይሰማህ። እያዳመጥከው እንዳለ እንዲያውቅ አድርግ፤ እንዲሁም በርኅራኄ ያዘው። ስሜቱን ለመረዳት ጥረት አድርግ፤ እንዲሁም የራስህ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ ወይም በእሱ ላይ ለመፍረድ አትቸኩል። ሳያስበው በኋላ የሚጸጽተውን ነገር ሊናገር እንደሚችል አስታውስ።—ኢዮብ 6:2, 3

“የተጨነቁትን አጽናኗቸው።”—1 ተሰሎንቄ 5:14

ጓደኛህ በጭንቀት ሊዋጥ ወይም የከንቱነት ስሜት ሊሰማው ይችላል። ምን ብለህ መናገር እንዳለብህ ግራ ቢገባህም እንኳ እንደምታስብለት መግለጽህ ብቻ ሊያጽናናውና ሊያበረታታው ይችላል።

“እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው።”—ምሳሌ 17:17

ተግባራዊ እርዳታ ስጠው። በመሰለህ መንገድ እርዳታ ከመስጠት ይልቅ ምን እንድታደርግለት እንደሚፈልግ ጠይቀው። ጓደኛህ ምን እንደሚያስፈልገው መናገር ከከበደው አብራችሁ በሆነ እንቅስቃሴ መካፈል እንደምትችሉ ንገረው፤ ለምሳሌ ‘በእግራችን ዞር ዞር እንበል’ ልትለው ትችላለህ። አሊያም ደግሞ ገበያ በመውጣት፣ ቤት በማጽዳት ወይም በሌላ ሥራ ልታግዘው እንደምትችል ንገረው።—ገላትያ 6:2

‘በትዕግሥት ያዟቸው።’—1 ተሰሎንቄ 5:14

ጓደኛህ አንዳንድ ጊዜ ማውራት ላይፈልግ ይችላል። ስለዚህ ማውራት በሚፈልግበት ጊዜ ልታዳምጠው ፈቃደኛ እንደሆንክ ንገረው። ጓደኛህ በሕመሙ የተነሳ የሚጎዳህ ነገር ሊናገር ወይም ሊያደርግ ይችል ይሆናል። ቀጠሮ ሊሰርዝብህ ወይም በቀላሉ ሊበሳጭ ይችላል። የሚያስፈልገውን ድጋፍ በምትሰጥበት ወቅት ታጋሽ ለመሆንና ስሜቱን ለመረዳት ጥረት አድርግ።—ምሳሌ 18:24

የምትሰጠው እርዳታ ለውጥ ያመጣል

“ጓደኛዬ በማንኛውም ጊዜ ላዳምጣት ፈቃደኛ እንደሆንኩ እንድትተማመን እፈልጋለሁ። ለችግሮቿ መፍትሔ መስጠት ባልችልም ስትናገር በጥሞና አዳምጣታለሁ። አንዳንድ ጊዜ ሰሚ ጆሮ ማግኘቷ ብቻውን ቀለል እንዲላት ይረዳታል።”—ከአመጋገብ ችግር፣ ከጭንቀትና ከድባቴ ጋር የምትታገል ጓደኛ ያለቻት ፋራህa

አንዲት ወጣት የአንዲት አረጋዊት እጅ በርኅራኄ ይዛ።

“ጓደኛዬ በጣም ደግና አዎንታዊ ነች። ቤቷ ጣፋጭ ምግብ ጋበዘችኝ። ያሳየችኝ ፍቅር ስሜቴን አውጥቼ መግለጽ ቀላል እንዲሆንልኝ አድርጓል። ይህ ደግሞ በእጅጉ አበረታቶኛል።”—ከከባድ ድባቴ ጋር የምትታገለው ሃእን

“ትዕግሥት በጣም አስፈላጊ ነው። ባለቤቴ የሚያበሳጨኝ ነገር ስታደርግ ድርጊቷ የሕመሟ እንጂ የእውነተኛ ማንነቷ መገለጫ እንዳልሆነ ለማስታወስ እሞክራለሁ። ይህም እንዳልቆጣ እንዲሁም በአሳቢነት እንድይዛት ይረዳኛል።”—ከከባድ ድባቴ ጋር የምትታገል ሚስት ያለችው ጄኮብ

“ባለቤቴ በእጅጉ ትደግፈኛለች፤ እንዲሁም ታጽናናኛለች። በጭንቀት በምዋጥበት ጊዜ የማልፈልገውን ነገር እንዳደርግ አትጫነኝም። በዚህ የተነሳ የምትፈልገውን ነገር ማድረግ የማትችልባቸው ጊዜያት ይኖራሉ። የምታሳየው የራስን ጥቅም የመሠዋት መንፈስና ልግስና በእጅጉ ረድቶኛል።”—ከጭንቀት ጋር የሚታገለው ኤንሪኮ

a አንዳንዶቹ ስሞች ተቀይረዋል።

ለተጨማሪ እርዳታ፦

በጥቅምት 2015 ንቁ! ላይ የወጣውን “የምንወደው ሰው ሲታመም” የሚለውን ርዕስ ከ​jw.org ላይ አንብብ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ