የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w25 የካቲት ገጽ 32
  • በተቃውሞ ውስጥ ድፍረት ማሳየት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በተቃውሞ ውስጥ ድፍረት ማሳየት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለሚያገለግሉት ሁሉ ወሮታ ከፋይ የሆነ አምላክ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • እንደ ኤርምያስ በንቃት ተጠባበቁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ይሖዋ ኤርምያስን እንዲሰብክ ላከው
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ደፋር ሁኑ​—ይሖዋ ከእናንተ ጋር ነው!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
w25 የካቲት ገጽ 32

የጥናት ፕሮጀክት

በተቃውሞ ውስጥ ድፍረት ማሳየት

ኤርምያስ 38:1-13⁠ን አንብብ፤ ከዚያም ከነቢዩ ኤርምያስና ከጃንደረባው ኤቤድሜሌክ ስለ ድፍረት ተማር።

አውዱን መርምር። ኤርምያስ የይሖዋን መልእክት ሲያውጅ ድፍረት ያሳየው እንዴት ነው? (ኤር. 27:12-14፤ 28:15-17፤ 37:6-10) ሰዎቹ መልእክቱን ሲሰሙ ምን ምላሽ ሰጡ?—ኤር. 37:15, 16

በጥልቀት ምርምር አድርግ። ኤርምያስ ምን ዓይነት ተቃውሞ አጋጥሞታል? (jr-E 26-27 አን. 20-22) በጥንት ዘመን ስለነበሩ የውኃ ጉድጓዶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሞክር። (it-1-E 471) ኤርምያስ ጉድጓድ ውስጥ ተጥሎ ጭቃ ውስጥ ሲሰምጥ ምን ተሰምቶት የነበረ ይመስልሃል? ኤቤድሜሌክን ምን አስፈርቶት ሊሆን ይችላል?—w12 5/1 31 አን. 2-3

ትምህርቱን ለማስተዋል ሞክር። ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • ይህ ዘገባ ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹን ስለሚጠብቅበት መንገድ ምን ያስተምረኛል? (መዝ. 97:10፤ ኤር. 39:15-18)

  • ድፍረት ማሳየት የሚያስፈልገኝ በየትኞቹ ሁኔታዎች ውስጥ ነው?

  • ተቃውሞ ሲያጋጥመኝ ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ ድፍረት ማዳበር የምችለው እንዴት ነው? (w11 3/1 30)a

a የጥናት ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ተጨማሪ ሐሳብ ለማግኘት በሐምሌ 2023 መጠበቂያ ግንብ ላይ የወጣውን “ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ