ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች
መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ለማንበብ ምን ይረዳሃል?
ሕይወትህ ሩጫ የበዛበት በመሆኑ የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ማንበብ ይከብድሃል? (ኢያሱ 1:8) ከሆነ የሚከተሉትን ምክሮች በሥራ ላይ ለማዋል ሞክር፦
ዕለታዊ ማስታወሻ ሙላ። መጽሐፍ ቅዱስን እንድታነብ የሚያስታውስ አላርም በኤሌክትሮኒክ መሣሪያህ ላይ ሙላ።
መጽሐፍ ቅዱስህን በቀላሉ የሚታይ ቦታ ላይ አስቀምጠው። የምታነበው የታተመውን መጽሐፍ ቅዱስ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስህን በየቀኑ በቀላሉ ልታየው የምትችልበት ቦታ ላይ አስቀምጠው።—ዘዳ. 11:18
የድምፅ ቅጂ አዳምጥ። የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴህን ስታከናውን በድምፅ የተቀዳውን መጽሐፍ ቅዱስ አዳምጥ። ታራ አቅኚና የልጆች እናት ከመሆኗም በተጨማሪ የምትሠራው በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ ነው። ታራ እንዲህ ብላለች፦ “የቤት ውስጥ ሥራዎችን እያከናወንኩ በድምፅ የተቀዳውን መጽሐፍ ቅዱስ ማዳመጤ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቤን ቋሚ ለማድረግ ረድቶኛል።”
ተስፋ አትቁረጥ። ያልተጠበቀ ሁኔታ ፕሮግራምህን ካስተጓጎለብህ ከመተኛትህ በፊት ቢያንስ ጥቂት ቁጥሮችን አንብብ። በየቀኑ ጥቂት ቁጥሮችን እንኳ ማንበብ በጣም ጠቃሚ ነው።—1 ጴጥ. 2:2