የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwyp ርዕስ 99
  • ሕሊናዬን ማሠልጠን የምችለው እንዴት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሕሊናዬን ማሠልጠን የምችለው እንዴት ነው?
  • የወጣቶች ጥያቄ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሕሊና ምንድን ነው?
  • ሕሊናህን ማሠልጠን ያለብህ ለምንድን ነው?
  • ሕሊናህን ማሠልጠን የምትችለው እንዴት ነው?
  • ጥሩ ሕሊና ይዘህ መኖር የምትችለው እንዴት ነው?
    ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
  • በአምላክ ፊት ጥሩ ሕሊና መያዝ
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
  • ሕሊናህ በሚገባ ሠልጥኗል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • ሕሊናችሁ አስተማማኝ መሪ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የወጣቶች ጥያቄ
ijwyp ርዕስ 99
አንድ ወጣት ውሳኔ ሲያደርግ። ከበስተ ጀርባ ያሉት ቀስቶች ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር ያመለክታሉ።

የወጣቶች ጥያቄ

ሕሊናዬን ማሠልጠን የምችለው እንዴት ነው?

ሕሊናህ ከምን ጋር ሊመሳሰል ይችላል?

  • ከኮምፓስ?

  • ከመስተዋት?

  • ከጓደኛ?

  • ከዳኛ?

አራቱም መልሶች ናቸው። እንዲህ የምንለው ለምን እንደሆነ ይህ ርዕስ ያብራራል።

  • ሕሊና ምንድን ነው?

  • ሕሊናህን ማሠልጠን ያለብህ ለምንድን ነው?

  • ሕሊናህን ማሠልጠን የምትችለው እንዴት ነው?

  • እኩዮችህ ምን ይላሉ?

ሕሊና ምንድን ነው?

ሕሊና ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ነገር ለመለየት የሚረዳ ችሎታ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሕሊና ‘በልብ ላይ እንደተጻፈ ሕግ’ እንደሆነ ይናገራል። (ሮም 2:15) ጥሩ ሕሊና ልታደርገው ያሰብከውን ወይም ያደረግከውን ውሳኔ እንድትገመግም ይረዳሃል።

  • ሕሊና እንደ ኮምፓስ ነው። ችግር ውስጥ እንዳትገባ ወደ ትክክለኛው መንገድ ይመራሃል።

  • ሕሊና እንደ መስተዋት ነው። ያለህን የሥነ ምግባር አቋምና ምን ዓይነት ሰው እንደሆንክ ያሳይሃል።

  • ሕሊና እንደ ጥሩ ጓደኛ ነው። ከሰማኸው ስኬታማ እንድትሆን የሚረዳ ጥሩ ምክር ይሰጥሃል።

  • ሕሊና እንደ ዳኛ ነው። መጥፎ ነገር ስታደርግ ይፈርድብሃል።

አንድ ወጣት የትኛውን የቪዲዮ ጌም እንደሚመርጥ ለመወሰን ሲሞክር።

ጥሩ ሕሊና ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ ለማድረግ ይረዳሃል

ዋናው ነጥብ፦ ሕሊና (1) ጥሩ ውሳኔ እንድታደርግ እንዲሁም (2) ስህተትህን ማረም እንድትችል የሚረዳህ በጣም አስፈላጊ የሆነ መሣሪያ ነው።

ሕሊናህን ማሠልጠን ያለብህ ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ “ጥሩ ሕሊና ይኑራችሁ” በማለት ይመክረናል። (1 ጴጥሮስ 3:16) ሆኖም ሕሊናህ ካልሠለጠነ ጥሩ ሕሊና መያዝ ከባድ ይሆንብሃል።

“ወላጆቼ የት እንዳለሁ ሲጠይቁኝ እዋሻቸው ነበር። መጀመሪያ አካባቢ ሕሊናዬ ይረብሸኝ ነበር፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን ይህ ስሜት ጠፋ።”—ጄኒፈር

በኋላ ላይ የጄኒፈር ሕሊና ለወላጆቿ እውነቱን እንድትነግራቸውና እነሱን ማታለሏን እንድታቆም አነሳስቷታል።

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ የጄኒፈር ሕሊና መቼ ቢያስጠነቅቃት ይሻል ነበር?

“ሁለት ዓይነት ሕይወት መምራት ከባድና ውጥረት የሚፈጥር ነገር ነው። ሕሊናችሁ አንድ ጊዜ መጥፎ ውሳኔ እንድታደርጉ ከፈቀደላችሁ ሌላ ጊዜ መጥፎ ውሳኔ ማድረግ እየቀለላችሁ ይመጣል።”—ማቲው

አንዳንድ ሰዎች ሕሊናቸውን ከናካቴው መስማት ያቆማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው እነዚህ ሰዎች ‘የሥነ ምግባር ስሜታቸው ደንዝዟል።’ (ኤፌሶን 4:19) አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ይህን ሐረግ “የኀፍረት ስሜታቸው በሙሉ ጠፍቷል” በማለት ተርጉሞታል።

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ መጥፎ ነገር ቢሠሩም የጥፋተኝነት ስሜት የማይሰማቸው ሰዎች ሕይወታቸው የተሻለ የሚሆን ይመስልሃል? እነዚህ ሰዎች ወደፊት ምን ዓይነት ችግር ያጋጥማቸዋል?

ዋናው ነጥብ፦ ጥሩ ሕሊና እንዲኖርህ ‘ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር ለመለየት የማስተዋል ችሎታህን በማሠራት ማሠልጠን’ ያስፈልግሃል።—ዕብራውያን 5:14

ሕሊናህን ማሠልጠን የምትችለው እንዴት ነው?

ሕሊናህን ለማሠልጠን የራስህን ድርጊት ከአንድ መሥፈርት ጋር ልታወዳድር ይገባል። አንዳንዶች፣ ሌሎች ሰዎች ባወጧቸው መሥፈርቶች ይመራሉ፤ ለምሳሌ

  • ቤተሰባቸው ወይም ማኅበረሰቡ

  • እኩዮቻቸው

  • ታዋቂ ሰዎች

ሆኖም የመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርት እነዚህ ሰዎች ከሚያወጡት መሥፈርት በእጅጉ የላቀ ነው። ደግሞም ይህ መሆኑ አያስገርምም፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው “በአምላክ መንፈስ መሪነት” ነው፤ አምላክ ደግሞ ፈጣሪያችን ከመሆኑም ሌላ ለእኛ የሚበጀን ምን እንደሆነ ያውቃል።—2 ጢሞቴዎስ 3:16

እስቲ አንዳንድ ምሳሌዎችን እንመልከት።

መሥፈርት፦ “በሁሉም ነገር በሐቀኝነት ለመኖር እንፈልጋለን።”—ዕብራውያን 13:18

  • ፈተና ላይ ለመኮረጅ፣ ወላጆችህን ለመዋሸት ወይም ለመስረቅ ስትፈተን ይህ መሥፈርት ሕሊናህን ለማሠልጠን የሚረዳህ እንዴት ነው?

  • ሕሊናህ በሁሉም ነገር ሐቀኛ እንድትሆን የሚገፋፋህ ከሆነ አሁንም ሆነ ወደፊት ምን ጥቅም የምታገኝ ይመስልሃል?

መሥፈርት፦ “ከፆታ ብልግና ሽሹ።”—1 ቆሮንቶስ 6:18

  • ፖርኖግራፊ ለማየት ወይም ከጋብቻ በፊት የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ስትፈተን ይህ መሥፈርት ሕሊናህን ለማሠልጠን የሚረዳህ እንዴት ነው?

  • ሕሊናህ ከፆታ ብልግና እንድትሸሽ የሚገፋፋህ ከሆነ አሁንም ሆነ ወደፊት ምን ጥቅም ታገኛለህ?

መሥፈርት፦ “አንዳችሁ ለሌላው ደጎችና ከአንጀት የምትራሩ ሁኑ፤ . . . እርስ በርሳችሁ በነፃ ይቅር ተባባሉ።”—ኤፌሶን 4:32

  • ከወንድምህ፣ ከእህትህ ወይም ከጓደኛህ ጋር በምትጣላበት ጊዜ ይህ መሥፈርት ሕሊናህን ለማሠልጠን የሚረዳህ እንዴት ነው?

  • ሕሊናህ መሐሪና ሩኅሩኅ እንድትሆን የሚገፋፋህ ከሆነ አሁንም ሆነ ወደፊት ምን ጥቅም ታገኛለህ?

መሥፈርት፦ “ይሖዋ . . . ዓመፅን የሚወድን ማንኛውንም ሰው ይጠላል።”—መዝሙር 11:5

  • ፊልም፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ወይም ቪዲዮ ጌም በምትመርጥበት ጊዜ ይህ መሥፈርት የሚረዳህ እንዴት ነው?

  • ሕሊናህ ዓመፅ ከሚንጸባረቅበት መዝናኛ እንድትርቅ የሚገፋፋህ ከሆነ አሁንም ሆነ ወደፊት ምን ጥቅም ታገኛለህ?

እውነተኛ ታሪክ፦ “ጓደኞቼ ዓመፅ የሚንጸባረቅበት የቪዲዮ ጌም ይጫወቱ ነበር፤ እኔም እጫወት ነበር። በኋላ ግን አባቴ እነዚህን ጌሞች እንዳልጫወት ከለከለኝ። ስለዚህ ጓደኞቼ ቤት ስሄድ ብቻ መጫወት ጀመርኩ። ወደ ቤት ስመለስ ምን ሳደርግ እንደቆየሁ አልናገርም ነበር። አባቴ ‘ምን ሆነሃል?’ ብሎ ሲጠይቀኝ ‘ምንም አልሆንኩም’ እለው ነበር። አንድ ቀን ግን መዝሙር 11:5⁠ን ሳነብ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ። እነዚያን ጌሞች መጫወት እንደሌለብኝ ገባኝ። ከዚያም መጫወቴን አቆምኩ። አንዱ ጓደኛዬም የእኔን ምሳሌ በመከተል ዓመፅ የሚንጸባረቅባቸው ጌሞችን መጫወት አቆመ።”—ጄረሚ

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ የጄረሚ ሕሊና መሥራት የጀመረው መቼ ነው? ጄረሚ ሕሊናውን መስማት የጀመረውስ መቼ ነው? ከጄረሚ ታሪክ ምን ትማራለህ?

ዋናው ነጥብ፦ ሕሊናችን ምን ዓይነት ሰው እንደሆንንና ትልቅ ቦታ የምንሰጠው ለምን ነገር እንደሆነ ያሳያል። ሕሊናህ ስለ አንተ ምን ይናገር ይሆን?

እኩዮችህ ምን ይላሉ?

አሌክሲስ።

“ሕሊናችን ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር መለየት ይችላል ማለት ምንጊዜም ትክክል የሆነውን ነገር እናደርጋለን ማለት አይደለም። በትክክል የሚሠራ ኮምፓስ በየት በኩል መሄድ እንዳለብን ሊጠቁመን ይችላል፤ በዚያ መንገድ ለመሄድ የምንወስነው ግን እኛ ነን።”—አሌክሲስ

ላዮኔል።

“ሕሊና መውጫ የሚያሳጣ አጥር አይደለም። ከዚህ ይልቅ መሄድ ወደምንፈልግበት ቦታ የሚወስድ መንገድ ነው። ሕሊናችን ወደፊት ሊያጋጥሙን ከሚችሉ አደጋዎች እንድንርቅ የሚረዱ ምልክቶች አሉት።”—ላዮኔል

ኢዛቤላ።

“በሌላ ሰው ሕሊና ተመርቼ ውሳኔ ማድረግ እንደሌለብኝ ተምሬያለሁ። ሕሊናዬ በደንብ የሠለጠነ ሰለሆነ አንድን ነገር ማድረግ እንደሌለብኝ ከተሰማኝ በቂ ምክንያት አለኝ ማለት ነው። ሌሎችን ለማስደሰት ብዬ የምመራበትን መሥፈርት ልቀይር አይገባም።”—ኢዛቤላ

ክለሳ፦ ሕሊናዬን ማሠልጠን የምችለው እንዴት ነው?

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶች በእጅጉ የላቁ እንደሆኑ አስታውስ። መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በአምላክ መንፈስ መሪነት ነው፤ አምላክ ደግሞ ፈጣሪያችን ከመሆኑም ሌላ ለእኛ የሚበጀን ምን እንደሆነ ያውቃል።

  • ሕሊናህን ከመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶች ጋር አወዳድር። እንደ አምላክ ዓይነት አስተሳሰብ ማዳበር እንድትችል ማሻሻያ ማድረግ ያለብህ በየትኞቹ አቅጣጫዎች ነው?

  • በመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶች ተመራ። በመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶች ተጠቅመህ የዕለት ተዕለት ውሳኔዎችን አድርግ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ