የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mrt ርዕስ 45
  • ሩሲያ ዩክሬንን ወረረች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሩሲያ ዩክሬንን ወረረች
  • ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እነዚህ ክንውኖች እንደሚከሰቱ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል?
  • ነገ ሁኔታዎች እንደሚሻሻሉ ተስፋ ማድረግ እንችላለን?
  • በዛሬው ጊዜ ‘የሰሜኑ ንጉሥ’ ማን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
  • ሃይማኖትና የዩክሬን ጦርነት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • የዩክሬን ጦርነት ሁለተኛ ዓመቱን ያዘ—መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ተስፋ አለ?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ‘የሰሜኑ ንጉሥ’ በፍጻሜው ዘመን
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
ለተጨማሪ መረጃ
ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
mrt ርዕስ 45
ዩክሬንን እና አጎራባች አገራትን የሚያሳይ ካርታ።

ነቅታችሁ ጠብቁ!

ሩሲያ ዩክሬንን ወረረች

የካቲት 24, 2022 ሊነጋጋ አካባቢ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ ወረራ ጀመረች፤ ይህ የሆነው የዓለም መሪዎች ጦርነቱን ለማስቀረት እየተረባረቡ በነበሩበት ወቅት ነው። ይህ ግጭት በቀረው ዓለም ላይ ምን ተጽዕኖ ይኖረው ይሆን? የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከጥቂት ቀናት በፊት እንዲህ ብለው ነበር፦ “ይህ በንጹሐን ሰዎች ላይ የሚያስከትለውን መከራ፣ ጥፋትና ውድመት እንዲህ ብሎ ለመገመት እንኳ ያዳግታል፤ ስጋቱ ለአውሮፓ ብቻ ሳይሆን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ይተርፋል።”

እነዚህ ክንውኖች እንደሚከሰቱ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል?

  • ኢየሱስ ክርስቶስ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳል” በማለት ትንቢት ተናግሯል። (ማቴዎስ 24:7) በዛሬው ጊዜ የሚነሱት ጦርነቶች የኢየሱስ ትንቢት እየተፈጸመ እንደሆነ ያሳያሉ፤ ለዚህ ማስረጃ ለማየት “‘የመጨረሻው ዘመን’ ምልክት ምንድን ነው?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኘው የራእይ መጽሐፍ ጦርነትን በምሳሌያዊ መንገድ ገልጾታል፤ ‘ደማቅ ቀይ ቀለም ባለው ፈረስ’ ላይ የተቀመጠ ጋላቢ ‘ሰላምን ከምድር እንደሚወስድ’ ይናገራል። (ራእይ 6:4) በዘመናችን ያሉት ጦርነቶች የዚህ ትንቢት ፍጻሜ ናቸው የምንለው ለምንድን ነው? “አራቱ ፈረሰኞች—እነማን ናቸው?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

  • የዳንኤል መጽሐፍ ‘በሰሜኑ ንጉሥ’ እና “በደቡቡ ንጉሥ” መካከል ሽኩቻ እንደሚኖር በትንቢት ተናግሯል። (ዳንኤል 11:25-45) ሩሲያ እና አጋሮቿ የሰሜኑ ንጉሥ ናቸው የምንለው ለምንድን ነው? ይህን ለማወቅ ፍጻሜውን ያገኘ ትንቢት—ዳንኤል ምዕራፍ 11 የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት።a

  • የራእይ መጽሐፍ ‘ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ታላቅ ቀን የሚካሄደው ጦርነት’ በማለት የሚገልጸው ጦርነትም አለ። (ራእይ 16:14, 16) ይህ ግን አሁን እያየነው እንዳለው በአገራት መካከል የሚነሳ ጦርነት አይደለም። ወደፊት የሚከሰተውን ይህን ጦርነት በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “የአርማጌዶን ጦርነት ምንድን ነው?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

ነገ ሁኔታዎች እንደሚሻሻሉ ተስፋ ማድረግ እንችላለን?

  • መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ “ጦርነትን ከመላው ምድር ላይ ያስወግዳል” ይላል። (መዝሙር 46:9) አምላክ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሰጠውን ተስፋ ማወቅ ትፈልጋለህ? “የተሻለ ጊዜ ይመጣል ብለን ተስፋ ማድረግ እንችላለን?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

  • ኢየሱስ፣ ተከታዮቹ ‘የአምላክ መንግሥት ይምጣ’ ብለው እንዲጸልዩ አስተምሯል። (ማቴዎስ 6:9, 10) ይህ መንግሥት በሰማይ የተቋቋመ መንግሥት ሲሆን ምድር ላይ የአምላክ ፈቃድ እንዲፈጸም ያደርጋል፤ ከአምላክ ፈቃድ መካከል ደግሞ ዓለም አቀፍ ሰላም ይገኝበታል። ይህ መንግሥት አንተን የሚጠቅም ምን ነገር ያደርጋል? ይህን ለማወቅ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት።

ዩክሬን ውስጥ ከ129,000 በላይ የይሖዋ ምሥክሮች ይገኛሉ። በሌሎች አገሮች እንዳሉት የይሖዋ ምሥክሮች ሁሉ እነሱም ፖለቲካ ውስጥ አይገቡም፣ በጦርነትም አይሳተፉም፤ እንዲህ በማድረግ የኢየሱስን ምሳሌ ይከተላሉ። (ዮሐንስ 18:36) በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ‘የአምላክን መንግሥት ምሥራች’ ማወጃቸውን ቀጥለዋል፤ ጦርነትን ጨምሮ ለሰው ልጅ ችግሮች መፍትሔው የአምላክ መንግሥት እንደሆነ ይሰብካሉ። (ማቴዎስ 24:14) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኘው የተስፋ መልእክት መማር ከፈለግህ እባክህ የይሖዋ ምሥክሮችን አነጋግር።

a ይህን ትንቢት በተመለከተ የተሟላ ማብራሪያ ለማግኘት “‘የሰሜኑ ንጉሥ’ በፍጻሜው ዘመን” እና “በዛሬው ጊዜ ‘የሰሜኑ ንጉሥ’ ማን ነው?” የሚሉትን ርዕሶች ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ