የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwfq ርዕስ 63
  • የይሖዋ ምሥክሮች ፀረ ክትባት ናቸው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የይሖዋ ምሥክሮች ፀረ ክትባት ናቸው?
  • ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የይሖዋ ምሥክሮች የሚሰጣቸውን የሕክምና እርዳታ ይቀበላሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • የምትመርጠው የሕክምና ዓይነት ለውጥ ያመጣልን?
    ንቁ!—2001
  • የይሖዋ ምሥክሮች ስለ ሕክምና ያላቸው አቋም ምንድን ነው?
    ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
  • ድንገት ለሚያጋጥም የጤና ችግር ከወዲሁ ተዘጋጁ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
ለተጨማሪ መረጃ
ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
ijwfq ርዕስ 63
ለክትባት የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች፦ ስሪንጅና ክትባት የያዙ ብልቃጦች።

የይሖዋ ምሥክሮች ፀረ ክትባት ናቸው?

አይደሉም። የይሖዋ ምሥክሮች ፀረ ክትባት አቋም የላቸውም። መከተብ ወይም አለመከተብ ለእያንዳንዱ ክርስቲያን የተተወ የግል ውሳኔ እንደሆነ እናምናለን። ብዙዎቹ የይሖዋ ምሥክሮች መከተብ ይመርጣሉ።

ጥሩ ሕክምና ማግኘት እንፈልጋለን፤ በተጨማሪም የሕክምናው ሳይንስ በከባድ በሽታ የመጠቃት አጋጣሚን ለመቀነስ የሚያደርጋቸውን የተለያዩ ጥረቶች እናደንቃለን። የሕክምና ባለሙያዎች፣ በተለይ ከባድ ቀውስ በሚፈጠርበት ወቅት ሌሎችን ለማገልገል ለሚያሳዩት ትጋትና ለሚከፍሉት መሥዋዕትነት በጣም አመስጋኞች ነን።

የይሖዋ ምሥክሮች ከጤና ጥበቃ ባለሥልጣናት ጋር ይተባበራሉ። የይሖዋ ምሥክሮች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ በዚህ ድረ ገጽ ላይ በመቶዎች በሚቆጠሩ ቋንቋዎች ያወጧቸውን ማሳሰቢያዎች እንደ ምሳሌ ማንሳት ይቻላል፤ ሰዎች በየአካባቢያቸው የሚሰጣቸውን የደህንነት መመሪያ እንዲከተሉ ሲያበረታቱ ቆይተዋል። ለምሳሌ አካላዊ ርቀትን መጠበቅን፣ መሰባሰብን፣ ከሌሎች ተገልሎ መቆየትን፣ እጅ መታጠብን፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግንና ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ ባለሥልጣናት የሚያወጧቸውን ደንቦች መከተል ያለውን አስፈላጊነት በተደጋጋሚ ገልጸዋል።—ሮም 13:1, 2

የይሖዋ ምሥክሮች የሚያወጧቸው ጽሑፎች፣ ለበርካታ አሥርተ ዓመታት የሚከተሉትን መርሆዎች ሲያራምዱ ቆይተዋል፦

  • ከሕክምና ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የግል ውሳኔዎች ናቸው።—ገላትያ 6:5

    “[ይህ መጽሔት] ይሄኛው መድኃኒት ወይም የሕክምና ዓይነት ከዚያኛው የተሻለ ነው የሚል ዓይነት አስተያየት አይሰጥም፤ አንባቢዎች አንድን ዓይነት ሕክምና እንዲከታተሉ የሚያበረታታ ሐሳብም አያቀርብም። ዓላማው፣ ያለውን መረጃ ማስቀመጥ ብቻ ነው፤ በዚያ ላይ ተመሥርቶ ውሳኔ ማድረግ የአንባቢው ኃላፊነት ነው።”—ንቁ! የካቲት 8, 1987 (እንግሊዝኛ)

    “‘እኔም ሆንኩ ልጆቼ ብንከተብ ይሻላል ወይስ አይሻልም?’ የሚለው ጥያቄ ለእናንተ የተተወ ውሳኔ ነው።”—ንቁ! ነሐሴ 22, 1965 (እንግሊዝኛ)

  • ለሕይወት ትልቅ ቦታ ስለምንሰጥ ጥሩ ሕክምና ለማግኘት ጥረት እናደርጋለን።—የሐዋርያት ሥራ 17:28

    “የይሖዋ ምሥክሮች፣ ላሉባቸው የጤና እክሎች መፍትሔ ለማግኘት የጤና ባለሙያዎችን ያማክራሉ። ለሕይወት ትልቅ ዋጋ ስለሚሰጡ ምክንያታዊና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚስማማ እስከሆነ ድረስ ሕይወትን ለማስቀጠል የቻሉትን ሁሉ ያደርጋሉ።”—መጠበቂያ ግንብ፣ ሐምሌ 1, 1975 (እንግሊዝኛ)

    “የይሖዋ ምሥክሮች የሚሰጣቸውን መድኃኒትም ሆነ የሕክምና እርዳታ በደስታ ይቀበላሉ። በተጨማሪም ጥሩ ጤንነት እንዲሁም ረጅም ዕድሜ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ። እንዲያውም በመጀመሪያው መቶ ዘመን እንደነበረው እንደ ሉቃስ አንዳንዶቹ ሐኪሞች ናቸው። . . . የይሖዋ ምሥክሮች የሕክምና እርዳታ የሚሰጡ ባለሙያዎች በትጋትና በሙሉ ልብ ለሚያከናውኑት ሥራ ከፍተኛ አድናቆት አላቸው። በተጨማሪም እነዚህ ባለሙያዎች ለታመሙ ሰዎች ለሚሰጡት እፎይታ አመስጋኞች ናቸው።”—መጠበቂያ ግንብ፣ የካቲት 1, 2011

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ