የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwyp ርዕስ 7
  • ትምህርት ቢያስጠላኝስ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትምህርት ቢያስጠላኝስ?
  • የወጣቶች ጥያቄ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ትምህርቴን ማቋረጥ ይኖርብኛልን?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች
  • ትምህርቴን ማቋረጥ ይኖርብኛል?
    ንቁ!—2010
  • ወደ ትምህርት ቤት እየሄድህ መማር ያለብህ ለምንድን ነው?
    ወጣትነትህን በተሻለ መንገድ ተጠቀምበት
  • ትምህርቴን ባቋርጥ ይሻል ይሆን?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1
ለተጨማሪ መረጃ
የወጣቶች ጥያቄ
ijwyp ርዕስ 7
በሐዘን የተዋጠ አንድ ወጣት ትምህርት ቤት ውስጥ ሎከሮች አጠገብ ቆሞ።

የወጣቶች ጥያቄ

ትምህርት ቢያስጠላኝስ?

የማያፈናፍኑ አስተማሪዎች። የእኩያ ተጽዕኖ። ከባድ ፈተናዎችና የቤት ሥራ ናዳ። አዎ፣ ትምህርት ቢያስጠላህ የሚያስገርም አይደለም።a ሬቸልb የተባለች ወጣት እንዲህ ብላለች፦

“ትምህርት ቤት ሂጂ ከምባል ሌላ የትም ቦታ ሂጂ ብባል ይቀለኛል። ባሕር ዳርቻ ብሄድ ወይም ከጓደኞቼ ጋር ብዝናና እመርጣለሁ፤ ሌላው ቢቀር ምግብ በማብሰል ወይም ቤት በማጽዳት ወላጆቼን ባግዝ ይሻለኛል!”

አንተም እንደ ሬቸል የሚሰማህ ከሆነ የትምህርት ቤት ሕይወትህ እስር ቤት ሊሆንብህና የምትፈታው ስትመረቅ እንደሆነ ሊሰማህ ይችላል። ይሁንና በትምህርት ቤት የምታሳልፈውን ጊዜ ከዚህ በተሻለ መንገድ ልትመለከተው ትችል ይሆን?

ይህን ታውቅ ነበር? ለትምህርት ያለህን አመለካከት ካስተካከልክ ትምህርት ቤት እስር ቤት አይሆንብህም። ከዚህ ይልቅ አዋቂ ስትሆን የሚያስፈልጉህን ክህሎቶች የምታዳብርበት ቦታ ይሆንልሃል።

ለትምህርት ያለህን አመለካከት ለማስተካከል በሚከተሉት ነገሮች ላይ ለማተኮር ሞክር፦

የማስታወሻ ደብተርና የእርሳስ ምልክት።

በምታገኘው ትምህርት ላይ አተኩር። ጎበዝ ተማሪ ከሆንክ ወደፊት በሥራ ቦታህም ሆነ በሌሎች የሕይወትህ ዘርፎች ችግሮች ሲያጋጥሙህ ሁልጊዜ የሌሎችን እርዳታ ከመጠየቅ ይልቅ በተሳካ ሁኔታ ልትወጣቸው ትችላለህ። ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ትምህርት እንዲያስጠላኝ የሚያደርጉ ነገሮች ቢኖሩም ከትምህርቴ ምን ጥቅም እያገኘሁ ነው?’

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ጥበብንና የማመዛዘን ችሎታን ጠብቅ።”​—ምሳሌ 3:21

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “የትምህርት ውጤቴ ዝቅተኛ ከሆነ ምን ላድርግ?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

የቼክ ሊስት ምልክት።

በልማዶችህ ላይ አተኩር። ከትምህርት ቤት ሕይወትህ ጊዜህን በአግባቡ መጠቀምን፣ በፕሮግራም መመራትን እንዲሁም ጥሩ የሥራ ልማድ ማዳበርን ልትማር ትችላለህ፤ እነዚህ ክህሎቶች አዋቂ ስትሆንም ይጠቅሙሃል። ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘የትምህርት ቤት ሕይወቴ በፕሮግራም እንድመራና ታታሪ ሠራተኛ እንድሆን የሚረዳኝ በየትኞቹ መንገዶች ነው? በዚህ ረገድ ምን ማሻሻያዎችን ላደርግ እችላለሁ?’

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “በትጋት ያከናወኑት ነገር ሁሉ ጥቅም ያስገኛል።”​—ምሳሌ 14:23

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “ጊዜዬን በአግባቡ መጠቀም የምችለው እንዴት ነው?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

እየተጨዋወቱ ያሉ ሁለት ሰዎች ምልክት።

ከሌሎች ጋር ባለህ ግንኙነት ላይ አተኩር፦ አብረውህ ከሚማሩ ልጆች ጋር ያለህ ግንኙነት የሌሎችን ስሜት ለመረዳትና ሌሎችን ለማክበር ሊረዳህ ይችላል። ጆሹዋ የተባለ ወጣት እንዲህ ብሏል፦ “ከሌሎች ጋር የሐሳብ ልውውጥ ማድረግን መማር ታሪክና ሳይንስ የመማርን ያህል አስፈላጊ ነው። ይህ ክህሎት በመላው ሕይወትህ ይጠቅምሃል።” ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘በትምህርት ቤት ሕይወቴ ከእኔ የተለየ አስተዳደግና እምነት ያላቸውን ጨምሮ ከሌሎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረኝ የሚረዳ ምን ትምህርት አግኝቻለሁ?’

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር ጥረት አድርጉ።”​—ዕብራውያን 12:14

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “ከሰዎች ጋር የመጨዋወት ችሎታዬን ማሻሻል የምችለው እንዴት ነው?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

መንገድ ላይ እየሄደ ያለ ሰው ምልክት።

በወደፊት ሕይወትህ ላይ አተኩር። ትምህርት ያለህን ችሎታ እንድታውቅና በዚያ ላይ ተመሥርተህ ግብ እንድታወጣ ይረዳሃል። ብሩክ የተባለች ወጣት እንዲህ ብላለች፦ “እንደ እኔ አንድ ሙያ ከተማርክ ስትመረቅ ሥራ ማግኘት ትችላለህ።” ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ከተመረቅኩ በኋላ ራሴን ማስተዳደር የምችለው እንዴት ነው? ያንን ክህሎት ከወዲሁ መማር የምችለውስ እንዴት ነው?’

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ለምታደርገው ነገር ሁሉ ዕቅድ ይኑርህ።”​—ምሳሌ 4:26 የ1980 ትርጉም

a በዚህ ርዕስ ውስጥ የተጠቀሱት አብዛኞቹ ሐሳቦች ከቤት ሆነው ለሚማሩ ወጣቶችም ይጠቅማሉ።

b አንዳንዶቹ ስሞች ተቀይረዋል።

እኩዮችህ ምን ይላሉ?

  • ማዲሰን።

    “ከተለያዩ ዓይነት ሰዎች ጋር በቡድን እንሠራለን። እንዲህ ስናደርግ ከእኔ የተለየ አስተዳደግና አኗኗር ያላቸውን ሰዎች ማዳመጥን ተምሬያለሁ። በጥቅሉ ሲታይ አብረውኝ የሚማሩት ልጆች በደግነትና በአክብሮት ይይዙኝ ነበር፤ ምክንያቱም ጥሩ ሰው እንደሆንኩና እንደማልተቻቸው ያውቃሉ።”—ማዲሰን

  • ራያን።

    “አብረውኝ ለሚማሩት ልጆች አዎንታዊ አመለካከት ማዳበርን ተምሬያለሁ። ብዙዎቹ ጥሩ ሰው ለመሆን ጥረት ያደርጋሉ። ስለዚህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚያበረታታ ሐሳብ ላካፍላቸው እሞክራለሁ።”—ራያን

  • ብሩክ።

    “ትምህርት ቤት ከሌሎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖርህ ይረዳሃል። አብረውህ ከሚማሩ ልጆች ጋር ቀኑን ሙሉ አብረህ ስለምትውል ምን ማለት እንዳለብህና ምን ማለት እንደሌለብህ እንዲሁም ትዕግሥተኛ መሆንና ያለህን ማካፈል የምትችለው እንዴት እንደሆነ ትማራለህ። በስፖርት ክፍለ ጊዜ የቡድን ጨዋታዎች ስላሉ በኅብረት መሥራትን ትማራለህ፤ ብቻህን ብትሆን ይህን ልትማር አትችልም።”—ብሩክ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ