የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 35
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ገና ምን ይላል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ገና ምን ይላል?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • ከገና በዓል ጋር የተያያዙ ነገሮች ታሪካዊ አመጣጥ
  • የገና በዓል በጃፓን አገር በጣም ተወዳጅ የሆነው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • የገና በዓል በምሥራቃውያን ዘንድ ሳይቀር የሚከበረው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ክርስቲያኖች ገናን ማክበር አለባቸው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • ገና ዓለማዊ በዓል ወይስ ሃይማኖታዊ በዓል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 35

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ገና ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ የተወለደበትን ቀን አይገልጽም፤ እንዲሁም ልደቱን ማክበር እንዳለብን አይናገርም። የማክሊንቶክ እና ስትሮንግ ሳይክሎፒዲያ “አምላክ የገና በዓል እንዲከበር አላዘዘም ወይም ገና መከበር እንዳለበት በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰ ነገር የለም” ይላል።

እንዲያውም የገና በዓል ታሪካዊ አመጣጥን በመመርመር ምንጩ የአረማውያን የአምልኮ ሥርዓት እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። አምላክን የምናመልከው እሱ በማይፈልገው መንገድ ከሆነ እንደሚያዝንብን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።​—ዘፀአት 32:5-7

ከገና በዓል ጋር የተያያዙ ነገሮች ታሪካዊ አመጣጥ

  1. የኢየሱስን ልደት ማክበር፦ “የጥንቶቹ ክርስቲያኖች የማንኛውንም ሰው የልደት በዓል ማክበርን አረማዊ ልማድ አድርገው ይመለከቱት ስለነበር [የኢየሱስን] ልደት አላከበሩም።”—ዘ ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፒዲያ

  2. ታኅሣሥ 29፦ ኢየሱስ በዚህ ቀን መወለዱን የሚያሳይ ምንም ዓይነት ማስረጃ የለም። የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ይህን ቀን የመረጡት በዓሉን በዚህ ሰሞን ወይም በቅዝቃዜው ወቅት ከሚከበሩ የአረማውያን በዓላት ጋር ለማያያዝ አስበው ሊሆን ይችላል።

  3. ስጦታ፣ ድግስና ግብዣ፦ ዚ ኢንሳይክሎፒዲያ አሜሪካና እንዲህ ይላል፦ “በገና በዓል ላይ ለሚንጸባረቁት ለአብዛኛዎቹ የፈንጠዝያ ልማዶች መሠረት የሆነው በታኅሣሥ አጋማሽ ላይ ይከበር የነበረው ሳተርናሊያ የተባለው የሮማውያን በዓል ነው። ለምሳሌ ያህል ትልቅ ድግስ ማዘጋጀት፣ ስጦታ መለዋወጥና ሻማ ማብራት ከዚህ በዓል የተወረሱ ልማዶች ናቸው።” ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ ደግሞ በሳተርናሊያ ወቅት “ሁሉም ሥራና የንግድ ቤቶች ይዘጉ ነበር” ብሏል።

  4. የገና መብራቶች፦ ኢንሳይክሎፒዲያ ኦቭ ሪሊጅን እንደተናገረው አውሮፓውያን ቤቶቻቸውን “በመብራትና በተለያዩ ዛፎች” የሚያስጌጡት የቅዝቃዜው ወቅት ማለፉን ለማክበርና ርኩስ መናፍስትን ለማባረር ነበር።

  5. የገና ዛፍ፦ “የዛፍ አምልኮ አረማውያን በሆኑ አውሮፓውያን ዘንድ የተለመደ ሲሆን ወደ ክርስትና ከተለወጡ በኋላም ቀጥሏል።” “በቀዝቃዛዎቹ ወራት አጋማሽ ላይ . . . የገና ዛፍን በበር ላይ ወይም በቤት ውስጥ የማስቀመጥ ልማድ” መኖሩ የዛፍ አምልኮ መቀጠሉን ያሳያል።​—ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ