የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwyp ርዕስ 47
  • ሐቀኛ መሆን ለምን አስፈለገ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሐቀኛ መሆን ለምን አስፈለገ?
  • የወጣቶች ጥያቄ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አንዳንዶች ሐቀኛ የማይሆኑበት ምክንያት
  • ሐቀኛ መሆን ምን ጥቅም ያስገኛል?
  • በሁሉም ነገር ሐቀኛ ሁን
    ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
  • በሁሉም ነገር ሐቀኞች ሁኑ
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
  • እውነተኝነት ዋጋ አለውን?
    ወጣትነትህን በተሻለ መንገድ ተጠቀምበት
  • በሁሉም ነገር ሐቀኛ ሁን
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
ለተጨማሪ መረጃ
የወጣቶች ጥያቄ
ijwyp ርዕስ 47
አንድ ልጅ ፈተና ላይ የመልስ ወረቀት ሲያቀብል

የወጣቶች ጥያቄ

ሐቀኛ መሆን ለምን አስፈለገ?

  • አንዳንዶች ሐቀኛ የማይሆኑበት ምክንያት

  • ሐቀኛ መሆን ምን ጥቅም ያስገኛል?

  • እኩዮችህ ምን ይላሉ?

አንዳንዶች ሐቀኛ የማይሆኑበት ምክንያት

በዘመናችን ብዙ ሰዎች ሐቀኛ መሆን ምንም ጥቅም እንደሌለው ይሰማቸዋል። እንዲያውም አንዳንዶች እንዲህ ሊሉ ይችላሉ፦

  • ‘ወላጆቼን ካልዋሸኋቸው ሊቀጡኝ ይችላሉ።’

  • ‘በዚህ ፈተና ላይ ካልኮረጅኩ ልወድቅ እችላለሁ።’

  • ‘ይህን ዕቃ ካልሰረቅኩ ዕቃውን ለመግዛት ገንዘብ ማጠራቀም ይኖርብኛል።’

ከዚህም በተጨማሪ አንዳንዶች ‘ምን ችግር አለው? ሁሉም ሰው ሐቀኝነት የጎደለው ተግባር ይፈጽም የለ?’ በማለት ሊጠይቁ ይችላሉ።

ያም ቢሆን ሐቀኝነት በጎደለው ተግባር የሚካፈለው ሁሉም ሰው አይደለም። በርካታ ወጣቶችን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ሐቀኛ መሆን ጥቅም እንደሚያስገኝ ይሰማቸዋል፤ ደግሞም እንዲህ ማሰባቸው ተገቢ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “አንድ ሰው ምንም ዘራ ምን ያንኑ መልሶ ያጭዳል” ይላል። (ገላትያ 6:7) ይህ ማለት የምናደርጋቸው ነገሮች ምንጊዜም ቢሆን ጥሩ ወይም መጥፎ ውጤት ይኖራቸዋል ማለት ነው።

ለምሳሌ፣ አንዳንዶች መዋሸታቸው ያስከተለባቸውን መጥፎ መዘዝ እንመልከት፦

“እናቴ፣ ከአንድ ልጅ ጋር አውርቼ እንደነበር ስትጠይቀኝ ዋሸሁ። ጉዳዩን በተመለከተ ግልጽ የሆነ መረጃ ስለነበራት እንደዋሸኋት ተረድታ ነበር። ስለ ልጁ ለሦስተኛ ጊዜ ስዋሻት በጣም ተናደደች። ለሁለት ሳምንት ያህል ከቤት ወጥቼ እንዳልዝናና የተቀጣሁ ሲሆን ለአንድ ወር ያህል ሞባይል ስልኬን እንዳልጠቀም እንዲሁም ቴሌቪዥን እንዳላይ ተከለከልኩ። ከዚያን ጊዜ ወዲህ ወላጆቼን ዋሽቼ አላውቅም!”—አኒታ

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ አኒታ፣ የእናቷን አመኔታ በድጋሚ ለማትረፍ ጊዜ ሊወስድባት የሚችለው ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “አሁን አታላይነትን ስላስወገዳችሁ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ።”—ኤፌሶን 4:25

“ወላጆቼን ዋሽቼ ማምለጥ የምችል መስሎኝ ነበር፤ ሆኖም ያወራሁትን ነገር በድጋሚ እንድነግራቸው ሲጠይቁኝ ያልጠበቅኩት ነገር ተከሰተ። የነገርኳቸው ነገር በጣም ከእውነት የራቀ ከመሆኑ የተነሳ አንዳንድ ዝርዝር ነገሮችን ማስታወስ አቃተኝ። መጀመሪያውኑ እውነቱን ከተናገራችሁ እንደዚህ ዓይነት ችግር ውስጥ አትገቡም!”—አንቶኒ

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ አንቶኒ እንዲህ ያለ አሳፋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳይገባ ምን ማድረግ ይችል ነበር?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ይሖዋ ውሸታም ከንፈሮችን ይጸየፋል፤ በታማኝነት የሚመላለሱ ግን ደስ ያሰኙታል።”—ምሳሌ 12:22

“ወሬ አዳምቃ ማውራት የምትወድ ጓደኛ አለችኝ። ነገሮች አጋንና ማውራት የምትወድ ከመሆኑም ሌላ ሰዎች ባላሰቡት መንገድ ነገሮችን ተርጉማ ልታወራ ትችላለች። ስለምወዳት በምታወራው ነገር ላይ ትኩረት ላለማድረግ እሞክራለሁ። ይሁንና እሷን ማመንም ሆነ በእሷ ላይ እምነት መጣል በጣም ይከብዳል።”—ኢቮን

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ የኢቮን ጓደኛ ነገሮችን አጋንና ማውራቷ ወይም “ጥቃቅን” ውሸቶችን መናገሯ ምን ዓይነት ስም አሰጥቷታል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “በሁሉም ነገር በሐቀኝነት ለመኖር እንፈልጋለን።”—ዕብራውያን 13:18

መሠረቱ የተሰነጠቀ ከጡብ የተሠራ ሕንፃ

በአንድ ሕንፃ መሠረት ላይ የሚፈጠር ስንጥቅ ጠቅላላ ሕንፃውን ሊያናጋ እንደሚችል ሁሉ ሐቀኝነት የጎደለው ተግባርም ጥሩ ስምህን ሊያጎድፍ ይችላል

ሐቀኛ መሆን ምን ጥቅም ያስገኛል?

አሁን ደግሞ ሐቀኛ መሆን የሚያስገኛቸውን አንዳንድ ጥቅሞች እንመልከት፦

“ከፊት ለፊቴ ትሄድ የነበረች አንዲት ሴት ገንዘብ ብትጥልም አላየችውም። በመሆኑም ጠርቼ ገንዘቡን ሰጠኋት። እሷም በጣም አመሰገነችኝ። ከዚያም ‘በጣም ጥሩ ሰው ነሽ። በሐቀኝነት እንዲህ የሚያደርግ ብዙ ሰው የለም’ አለችኝ። ትክክል የሆነውን ነገር አድርጎ መመስገን ጥሩ ስሜት ይፈጥራል!”—ቪቪየን

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ ይህቺ ሴት እንደዚህ ዓይነት የሐቀኝነት ድርጊት ማየቷ ያስገረማት ለምን ሊሆን ይችላል? ቪቪየን ሐቀኛ መሆኗ የጠቀማት እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ምንጊዜም ትክክል የሆነውን የሚያደርጉ ደስተኞች ናቸው።”—መዝሙር 106:3

“ቤተሰባችን በጽዳት ሥራ ላይ የተሰማራ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ቢሮዎችን ስናጸዳ ሳንቲም መሬት ላይ ወድቆ እናገኛለን። በዚህ ጊዜ ሳንቲሙን አንስተን አቅራቢያው ባለ ጠረጴዛ ላይ እናስቀምጣለን። ከሠራተኞቹ አንዷ በምናሳየው የሐቀኝነት ድርጊት ትበሳጭ ነበር። እንዲያውም አንድ ቀን ‘አሥር ሳንቲም እኮ ነው!’ አለችን። ያም ቢሆን ምንጊዜም ትተማመንብን ነበር።”—ጁሊያ

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ ጁሊያ፣ ሐቀኝነት በማሳየት ረገድ ያተረፈችው ስም ወደፊት ሌላ ሥራ ለመቀጠር የድጋፍ ደብዳቤ በሚያስፈልጋት ጊዜ ሊጠቅማት የሚችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ተቀባይነት ሊያገኝ እንደሚገባውና ምንም የሚያፍርበት ነገር እንደሌለው ሠራተኛ አድርገህ ራስህን በአምላክ ፊት ለማቅረብ የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ።”—2 ጢሞቴዎስ 2:15

“የሠራሁት 64 ሰዓት ቢሆንም የ80 ሰዓት የክፍያ ደረሰኝ ተሰጠኝ። ገንዘቡን ብወስደው ሊጠቅመኝ የሚችል ቢሆንም እንኳ እንደዛ አላደረግኩም። ሁኔታውን ለሒሳብ ክፍል ኃላፊዋ ሳሳውቃት በጣም አመሰገነችኝ። ምንም እንኳ ድርጅቱ አትራፊ ቢሆንም የተሰረቀ አድርጌ የምመለከተውን ገንዘብ ለማስቀረት አልፈለግኩም።”—ቤተኒ

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ ከአንድ ድርጅት ላይ መስረቅ ከአንድ ሰው ላይ ከመስረቅ ጋ ሲወዳደር ቀለል ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ይሖዋ ተንኮለኛን ሰው ይጸየፋልና፤ ከቅኖች ጋር ግን የጠበቀ ወዳጅነት አለው።”—ምሳሌ 3:32

እኩዮችህ ምን ይላሉ?

ቶቢ

ቶቢ

ተማሪዎች ከኩረጃ ጋር በተያያዘ የሚያደርጉት ጥረት በጣም ያስገርማል። ለመኮረጅ ከሚያደርጉት ጥረት ግማሽ ያህሉን እንኳ ቢያጠኑበት ኖሮ ፈተናውን ማለፍ በቻሉ ነበር!

ኦስትን

ኦስትን

‘እውነቱን ብናገር ሊያጋጥመኝ የሚችለው የከፋ ነገር ምንድን ነው?’ በማለት ራሴን እጠይቃለሁ። ከዚያም ብዋሽ ሊያጋጥመኝ ከሚችለው ችግር ጋር አወዳድረዋለሁ። መዘዞቹን አስቀድሜ ማሰቤ ሐቀኝነት የጎደለው ድርጊት እንዳልፈጽም ረድቶኛል።

ሀይዲ

ሀይዲ

ብዙ ሰዎች እውነቱን መናገር ችግር ሊያስከትልባቸው እንደሚችል ከተሰማቸው ይዋሻሉ። ሆኖም ዋሽቶ በጥፋተኝነት ስሜት ከመሠቃየት፣ እውነቱን ተናግሮ ቅጣቱን መቀበል ይሻላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ