የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 141
  • ምድር ትጠፋለች?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ምድር ትጠፋለች?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • የሰው ልጆች ምድርን ያጠፏት ይሆን?
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምድር በእሳት እንደምትጠፋ ያስተምራል?
  • ምድር
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • ይህ ዓለም ይጠፋል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ምድር ትጠፋ ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ምድር
    ንቁ!—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 141
ምድር ተበታትና ስትጠፋ

ምድር ትጠፋለች?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አትጠፋም። ምድር በእሳት ተቃጥላ አትጠፋም ወይም በሌላ ምድር አትተካም። መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ምድርን የፈጠራት ለዘላለም እንደሆነ ይናገራል።

  • “ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።”—መዝሙር 37:29

  • “[አምላክ] ምድርን በመሠረቶቿ ላይ መሠረታት፤ እሷም ለዘላለም ከቦታዋ አትናወጥም።”—መዝሙር 104:5

  • “ምድር ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።”—መክብብ 1:4

  • “[አምላክ] ምድርን የሠራትና ያበጃት፣ አጽንቶም የመሠረታት፣ መኖሪያ እንድትሆን እንጂ ለከንቱ [አይደለም]።”—ኢሳይያስ 45:18

የሰው ልጆች ምድርን ያጠፏት ይሆን?

የሰው ልጆች በአካባቢ ብክለት፣ በጦርነት አሊያም በሌሎች መንገዶች ምድርን እንዲያጠፏት አምላክ አይፈቅድላቸውም። እንዲያውም አምላክ “ምድርን እያጠፉ ያሉትን [ያጠፋቸዋል]።” (ራእይ 11:18) ግን ይህን የሚያደርገው እንዴት ነው?

አምላክ፣ ምድርን በተገቢው መንገድ መያዝ ያልቻሉትን የሰው ልጆች መንግሥታት አስወግዶ ፍጹም የሆነ ሰማያዊ መንግሥት በቦታቸው እንዲተካ ያደርጋል። (ዳንኤል 2:44፤ ማቴዎስ 6:9, 10) የዚህ መንግሥት ንጉሥ የአምላክ ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። (ኢሳይያስ 9:6, 7) ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት የተፈጥሮ ኃይሎችን መቆጣጠር እንደሚችል አሳይቷል። (ማርቆስ 4:35-41) ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ስለሆነ ምድርንም ሆነ በምድር ላይ ያሉትን የተፈጥሮ ኃይሎች ይቆጣጠራል። በምድር ላይ ያሉ ሁኔታዎች እንዲሻሻሉና እንዲስተካከሉ ያደርጋል፤ ይህም መላዋ ምድር የኤደን ገነት ዓይነት ቦታ እንድትሆን ያስችላል።—ማቴዎስ 19:28፤ ሉቃስ 23:43

መጽሐፍ ቅዱስ ምድር በእሳት እንደምትጠፋ ያስተምራል?

አያስተምርም። እንዲህ ያለው አስተሳሰብ የመጣው 2 ጴጥሮስ 3:7ን በተሳሳተ መንገድ ከመረዳት ነው፤ ጥቅሱ “ሰማያትም ሆኑ ምድር ለእሳት . . . ተጠብቀው ይቆያሉ” ይላል። ሆኖም ይህን ጥቅስ በትክክል ለመረዳት የሚከተሉትን ሁለት ነጥቦች መመልከት ያስፈልገናል፦

  1. መጽሐፍ ቅዱስ “ሰማያት”፣ “ምድር” እንዲሁም “እሳት” የሚሉትን ቃላት የተለያዩ ነገሮችን ለማመልከት ይጠቀምባቸዋል። ለምሳሌ ያህል፣ ዘፍጥረት 11:1 “ምድር ሁሉ አንድ ቋንቋና ተመሳሳይ ቃላት ትጠቀም ነበር” ይላል። በዚህ ጥቅስ ላይ “ምድር” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሰው ልጆችን በአጠቃላይ ነው።

  2. በ2 ጴጥሮስ 3:7 ዙሪያ ያለው ሐሳብ ሰማያት፣ ምድር እንዲሁም እሳት የሚሉት ቃላት ያላቸውን ትርጉም ለመረዳት ያስችላል። ቁጥር 5 እና 6 ይህ ትንቢት የሚፈጸምበትን ሁኔታ በኖኅ የጥፋት ውኃ ጊዜ ከነበረው ሁኔታ ጋር ያመሳስሉታል። በኖኅ ዘመን የነበረው ዓለም የጠፋ ቢሆንም ፕላኔታችን ግን አልጠፋችም። በዚያን ጊዜ የጠፋው “ምድር” የተባለው ዓመፀኛ የሆነው ማኅበረሰብ ነበር። (ዘፍጥረት 6:11) በዚያ ዘመን የነበሩት “ሰማያት” ይኸውም ማኅበረሰቡን ያስተዳድሩ የነበሩ ሰዎችም ጠፍተዋል። በመሆኑም በወቅቱ የጠፉት ክፉ ሰዎች እንጂ ምድር አልነበረችም። ኖኅና ቤተሰቡም ቢሆን በወቅቱ የነበረው ዓለም ሲጠፋ በሕይወት የተረፉ ሲሆን ከጥፋት ውኃው በኋላም ምድር ላይ ይኖሩ ነበር።—ዘፍጥረት 8:15-18

በጥፋት ውኃው ጊዜ እንደሆነው ሁሉ በ2 ጴጥሮስ 3:7 ላይ የተገለጸው ‘እሳትም’ የሚያጠፋው ግዑዟን ምድር ሳይሆን በውስጧ ያሉትን ክፉ ሰዎች ነው። አምላክ ‘ጽድቅ የሚሰፍንበት አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር’ እንደሚያመጣ ቃል ገብቷል። (2 ጴጥሮስ 3:13) ‘አዲሱ ምድር’ ማለትም አዲሱ ማኅበረሰብ ‘በአዲስ ሰማያት’ ይኸውም በአዲስ መንግሥት አገዛዝ ሥር ይተዳደራል። በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር ምድር ሰላም የሰፈነባት ገነት ትሆናለች።—ራእይ 21:1-4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ