የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 159
  • እንስሳት ወደ ሰማይ ይሄዳሉ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እንስሳት ወደ ሰማይ ይሄዳሉ?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • እንስሳት ነፍስ አላቸው?
  • ነፍስ ትሞታለች?
  • እንስሳት ኃጢአት ሊፈጽሙ ይችላሉ?
  • እንስሳትን በጭካኔ መያዝ ተገቢ ነው?
  • እንስሳት
    ንቁ!—2015
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • አምላክ ለእንስሳት ያስባል?
    ንቁ!—2011
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 159
ውሻ

እንስሳት ወደ ሰማይ ይሄዳሉ?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ምድር ላይ ብዙ ፍጥረታት ቢኖሩም ወደ ሰማይ የሚሄዱት ጥቂት ሰዎች ብቻ እንደሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። (ራእይ 14:1, 3) እነዚህ ሰዎች ወደ ሰማይ የሚሄዱት ነገሥታትና ካህናት ሆነው ከኢየሱስ ጋር ለመግዛት ነው። (ሉቃስ 22:28-30፤ ራእይ 5:9, 10) አብዛኞቹ ሰዎች ግን ከሞት ተነስተው ምድር ላይ በገነት ይኖራሉ።—መዝሙር 37:11, 29

መጽሐፍ ቅዱስ ውሾችን ጨምሮ የቤት እንስሳት ወደ ሰማይ እንደሚሄዱ አንድም ቦታ ላይ አይናገርም፤ ደግሞም ይህ የሆነበት በቂ ምክንያት አለ። እንስሳት “የሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች” ለመሆን የሚያስፈልገውን ብቃት ሊያሟሉ አይችሉም። (ዕብራውያን 3:1) ከእነዚህ ብቃቶች መካከል እውቀት፣ እምነትና የአምላክን ትእዛዛት መጠበቅ ይገኙበታል። (ማቴዎስ 19:17፤ ዮሐንስ 3:16፤ 17:3) ለዘላለም የመኖር ተስፋ ኖሯቸው የተፈጠሩት ሰዎች ብቻ ናቸው።—ዘፍጥረት 2:16, 17፤ 3:22, 23

ምድር ላይ ያሉ ፍጥረታት ወደ ሰማይ ለመሄድ ትንሣኤ ማግኘት ያስፈልጋቸዋል። (1 ቆሮንቶስ 15:42) መጽሐፍ ቅዱስ ከዚህ በፊት የተለያዩ ትንሣኤዎች እንደተከናወኑ ይገልጻል። (1 ነገሥት 17:17-24፤ 2 ነገሥት 4:32-37፤ 13:20, 21፤ ሉቃስ 7:11-15፤ 8:41, 42, 49-56፤ ዮሐንስ 11:38-44፤ የሐዋርያት ሥራ 9:36-42፤ 20:7-12) ያም ቢሆን ከሞት የተነሱት በሙሉ ሰዎች ናቸው፤ አንድም እንስሳ ከሞት እንደተነሳ የሚገልጽ ዘገባ አናገኝም።

  • እንስሳት ነፍስ አላቸው?

  • ነፍስ ትሞታለች?

  • እንስሳት ኃጢአት ሊፈጽሙ ይችላሉ?

  • እንስሳትን በጭካኔ መያዝ ተገቢ ነው?

እንስሳት ነፍስ አላቸው?

የላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሰዎችም ሆኑ እንስሳት ነፍስ እንደሆኑ ነው። (ዘኁልቁ 31:28) የመጀመሪያው ሰው አዳም ሲፈጠር ነፍስ አልተሰጠውም፤ ከዚህ ይልቅ እሱ ራሱ “ሕያው ነፍስ ሆነ።” (ዘፍጥረት 2:7 የግርጌ ማስታወሻ) ነፍስ ሲባል ሁለት ነገሮችን ይኸውም ‘የምድር አፈርን’ እና ‘የሕይወት እስትንፋስን’ የያዘ ነው።

ነፍስ ትሞታለች?

አዎ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ነፍስ እንደምትሞት ይናገራል። (ዘሌዋውያን 21:11 የግርጌ ማስታወሻ፤ ሕዝቅኤል 18:20) ሰዎችም ሆኑ እንስሳት ሲሞቱ ወደ ምድር አፈር ይመለሳሉ። (መክብብ 3:19, 20) በሌላ አባባል ከሕልውና ውጭ ይሆናሉ።

እንስሳት ኃጢአት ሊፈጽሙ ይችላሉ?

አይችሉም። ኃጢአት የሚባለው የአምላክን ትእዛዛት የሚጻረር ነገር ማሰብ ወይም መፈጸም ነው። አንድ ፍጥረት ኃጢአት ለመሥራት፣ የማሰብ ችሎታውን ተጠቅሞ ውሳኔ ማድረግ መቻል አለበት፤ እንስሳት ደግሞ እንዲህ ያለ ችሎታ የላቸውም። እንስሳት ውስን በሆነው የሕይወት ዘመናቸው ውስጥ አብዛኛውን ነገር የሚያደርጉት በደመ ነፍስ ነው። (2 ጴጥሮስ 2:12) ኃጢአት ባይሠሩም የሕይወት ዘመናቸው ሲያበቃ ይሞታሉ።

እንስሳትን በጭካኔ መያዝ ተገቢ ነው?

አይደለም። አምላክ ለሰዎች በእንስሳት ላይ ሥልጣን ሰጥቷቸዋል፤ ያም ቢሆን እነሱን የማሠቃየት መብት አልተሰጣቸውም። (ዘፍጥረት 1:28፤ መዝሙር 8:6-8) አምላክ ትናንሽ ወፎችን ጨምሮ ለእያንዳንዱ እንስሳ ያስባል። (ዮናስ 4:11፤ ማቴዎስ 10:29) ሕዝቦቹም እንስሳትን በደግነት እንዲይዙ ትእዛዝ ሰጥቷቸዋል።—ዘፀአት 23:12፤ ዘዳግም 25:4፤ ምሳሌ 12:10

ስለ እንስሳት የሚገልጹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ዘፍጥረት 1:28፦ “አምላክ [የመጀመሪያዎቹን ሰዎች] ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ ‘ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት፤ ግዟትም። እንዲሁም የባሕር ዓሣዎችን፣ በሰማያት ላይ የሚበርሩ ፍጥረታትንና በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረታትን በሙሉ ግዟቸው።’”

ትርጉሙ፦ አምላክ ለሰዎች በእንስሳት ላይ ሥልጣን ሰጥቷቸዋል።

ዘኁልቁ 31:28፦ “ግብር እንዲሆን በጦርነቱ ከተካፈሉት ተዋጊዎች ላይ ከሰውም ሆነ ከከብት፣ ከአህያም ሆነ ከመንጋ ከ500 አንድ ነፍስ ውሰድ።”

ትርጉሙ፦ ሰዎችም ሆኑ እንስሳት ነፍስ ናቸው።

ምሳሌ 12:10፦ “ጻድቅ የቤት እንስሳቱን ይንከባከባል።”

ትርጉሙ፦ ጥሩ ሰዎች የቤት እንስሶቻቸውን ጨምሮ ሁሉንም እንስሳት በተገቢው መንገድ ይይዛሉ።

ማቴዎስ 10:29፦ “ሁለት ድንቢጦች የሚሸጡት አነስተኛ ዋጋ ባላት ሳንቲም አይደለም? ሆኖም ከእነሱ አንዷም እንኳ አባታችሁ ሳያውቅ መሬት ላይ አትወድቅም።”

ትርጉሙ፦ አምላክ ትናንሽ ወፎችን ጨምሮ ሁሉንም እንስሳት ይመለከታል፤ እንዲሁም ያስብላቸዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ