የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwwd ርዕስ 14
  • የሃግፊሽ ልፋጭ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሃግፊሽ ልፋጭ
  • ንድፍ አውጪ አለው?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዛጎል አልባ ቀንድ አውጣ የሚያመነጨው የሚያጣብቅ ዝልግልግ ፈሳሽ
    ንድፍ አውጪ አለው?
  • ሕይወት የተገነባበት አስደናቂ ሰንሰለት
    ንቁ!—2005
  • በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበሩ ቀለሞችና ጨርቆች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • መልስ የሚያሻቸው ሁለት ጥያቄዎች
    ንቁ!—2015
ለተጨማሪ መረጃ
ንድፍ አውጪ አለው?
ijwwd ርዕስ 14
አንድ ሃግፊሽ በባሕሩ ወለል አካባቢ ሲዋኝ።

ንድፍ አውጪ አለው?

የሃግፊሽ ልፋጭ

የሃግፊሽ ልፋጭ ለረጅም ጊዜ የሳይንቲስቶችን ቀልብ ሲስብ ቆይቷል። ለምን? የሃግፊሽ ልፋጭ “በተፈጥሮ ከሚገኙ የሚለጠጡ ንጥረ ነገሮች መካከል የመጨረሻው ለስላሳ” እንደሆነ ይነገራል።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ሃግፊሽ በባሕር ወለል ላይ የሚኖር እባብ መሰል ዓሣ ነው። አዳኝ ዓሣ ሊበላው ሲሞክር ሃግፊሹ ለየት ካሉ ዕጢዎቹ ውስጥ ዝልግልግ ፈሳሽ ያመነጫል። ይህ ፈሳሽ ልፋጭ የሚፈጥሩ ፕሮቲኖችና በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ረጃጅም የፕሮቲን ክሮች አሉት። እነዚህ ፕሮቲኖች በሃግፊሹ ዙሪያ ያለውን ውኃ ወደ ልፋጭ ይቀይሩታል። ይህ ልፋጭ የአዳኙን ዓሣ የመተንፈሻ አካል ስለሚደፍነው ዓሣው ሃግፊሹን ተፍቶ ከአካባቢው ይሸሻል።

የሃግፊሽ ልፋጭ አስደናቂ ተፈጥሮ አለው። እያንዳንዱ የፕሮቲን ክር ከሰው ፀጉር በመቶ እጥፍ ይቀጥናል፤ ሆኖም ጥንካሬው ከናይለን ክር በአሥር እጥፍ ይበልጣል። የፕሮቲን ክሮችን የያዘው ዝልግልግ ፈሳሽ ወደ ባሕሩ ውኃ ሲለቀቅ ወንፊት መሰል ነገር ይሠራል። ይህ ወንፊት መሰል ነገር ከራሱ ክብደት 26,000 እጥፍ የሚበልጥ ክብደት ያለው ውኃ መያዝ ይችላል። እንዲያውም የሃግፊሽ ልፋጭ ሙሉ በሙሉ ከውኃ የተሠራ ነው ሊባል ይችላል።

ሳይንቲስቶች ከሃግፊሽ ልፋጭ ጋር የሚመሳሰል ነገር መሥራት አልቻሉም። አንድ ተመራማሪ እንደተናገሩት “ይህ ተፈጥሯዊ ንድፍ በጣም ውስብስብ ነው።” ያም ቢሆን ሳይንቲስቶች እነዚህን የፕሮቲን ክሮች ባክቴሪያ በመጠቀም ለማባዛት ያስባሉ። ዓላማቸው ቀላል፣ የማይቀደድ፣ የሚለጠጥ እና በተፈጥሯዊ መንገድ የሚበሰብስ ንጥረ ነገር መሥራት ነው። ሰው ሠራሽ የፕሮቲን ክሮች ረጅም ጊዜ የሚቆዩ ጨርቆችን እና የሕክምና ቁሳቁሶችን ለማዘጋጀት እንደሚያስችሉ ይገመታል። በእርግጥም ሰው ሠራሽ ልፋጭ ለተለያዩ አገልግሎቶች ሊውል ይችላል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ውስብስብ የሆነው የሃግፊሽ ልፋጭ በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ