የግርጌ ማስታወሻ
b ላክቴስ የተሰኘው ኤንዛይም፣ የኤንዛይም ጉድለት ለሚያስከትለው ሁኔታ ጥሩ ምሳሌ ይሆነናል። የላክቴስ ችግር ያለባቸው ሰዎች በወተት ውስጥ የሚገኘው ላክቶስ ከሰውነታቸው ጋር መዋሃድ ስለማይችል ወተት ሲጠጡ ይታመማሉ። ሌሎች ሰዎች ደግሞ በፎርማጆና በሌሎች ምግቦች ውስጥ የሚገኘውን ታይራሚን የተባለ ኬሚካል ወደ ጉልበት የሚለውጠው ኤንዛይም ጉድለት አለባቸው። በዚህም ሳቢያ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ዓይነቶቹን ምግቦች ሲመገቡ ገሚስ ራስምታት ሊይዛቸው ይችላል።