የግርጌ ማስታወሻ
a እሳት ማጥፊያ ብርድ ልብስ በአገርህ በብዛት የሚሠራበት ከሆነ አጠቃቀሙን በትክክል ጠንቅቀህ ማወቅ ይኖርብሃል። የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የእሳት አደጋ መከላከያ ማኅበር እንዲህ ሲል ገልጿል:- “እሳት ማጥፊያ ብርድ ልብሶች በሁለተኛ ደረጃ ሊታዩ የሚገባቸው ነገሮች መሆናቸው . . . መዘንጋት የለበትም። ልንጠቀምባቸው የሚገባው በቅርብ የሚገኙ ከሆነ ብቻ ነው። . . . የእሳት ማጥፊያ ብርድ ልብሱን በተሳሳተ መንገድ በመጠቀማችን የተነሳ ብርድ ልብሱ ጭሱን ወደ ፊታችን የሚለቀው ከሆነ ወይም እሳቱ ከጠፋ በኋላ ብርድ ልብሱ ካልተነሳ ጭሱና እሳቱ የሚያስከትሉትን ጉዳት የከፋ ሊያደርገው ይችላል።”