የግርጌ ማስታወሻ
a ዲስከቨር የተሰኘው መጽሔት እንደሚለው ከሆነ በሁሉም ሞገዶች ላይ የሚታየው ክብ ወይም ሞላላ ቅርጽ የተከተለ የውኃ እንቅስቃሴም ውኃው እየራቀ እንዲሄድ ሊያደርግ ይችላል። በውቅያኖስ ውስጥ የሚዋኙ ሰዎች ማዕበል እነሱ ጋር ከመድረሱ በፊት ውኃው እንደሚጎትታቸው ሆኖ ይሰማቸዋል። ሱናሚዎች በሚከሰቱበት ጊዜ ይህ ሁኔታ ጎላ ብሎ የሚታይ ሲሆን ይህም የመጀመሪያው ማዕበል ከመድረሱ በፊት የባሕር ዳርቻዎች ወይም ወደቦች እንዲደርቁ ያደርጋል።