የግርጌ ማስታወሻ b ዛሬም በተመሳሳይ አንዳንድ ክርስቲያኖች ቀጣሪዎች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ተቀጣሪዎች ናቸው። አንድ ክርስቲያን ቀጣሪ በሠራተኞቹ ላይ በደል እንደማያደርስ ሁሉ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርትም በባሪያዎቻቸው ላይ ከክርስቲያናዊ መሠረታዊ ሥርዓት ውጪ የሆነ ነገር እንደማያደርጉባቸው እርግጠኞች መሆን እንችላለን።—ማቴዎስ 7:12