የግርጌ ማስታወሻ
b ኒው ሳይንቲስት የተባለው መጽሔት ሪፖርት እንዳደረገው ከሆነ “አንድን ዓይነት አረም ማጥፊያ መቋቋም እንዲችሉ ተብለው ጀነቲካዊ ማስተካከያ የተደረገባቸው” የአውሮፓ ስኳር ድንቾች “እንዳጋጣሚ ሌላ ፀረ አረም ኬሚካልንም የመቋቋም ብቃት ኖሯቸው ተገኝተዋል።” ሌላ ዓይነት ፀረ አረም ኬሚካል እንዲቋቋም ተብሎ ከተዘጋጀ የስኳር ድንች ዓይነት ጋር ድንገት በመዳቀሉ እነዚህ ጂኖች ወደዚህኛው ተክል ገብተዋል። አንዳንድ ሳይንቲስቶች ፀረ አረም ኬሚካሎችን የመቋቋም አቅም ያላቸው የተለያዩ የእህል ዝርያዎች ጥቅም ላይ መዋላቸው ፀረ አረም ኬሚካሎችን የሚቋቋሙ አደገኛ አረሞች እንዲፈጠሩ ሊያደርግ ይችላል የሚል ስጋት አሳድሮባቸዋል።