የግርጌ ማስታወሻ
a እያንዳንዱ ሰው ለፅንስ መጨንገፍ የሚሰጠው ምላሽ ፈጽሞ የተለያየ መሆኑን ጥናታዊ ምርምሮች ያሳያሉ። አንዳንዶች ግራ ይጋባሉ፣ ሌሎች ይበሳጫሉ፣ ሌሎች ደግሞ በከባድ ሐዘን ይዋጣሉ። ተመራማሪዎች ሐዘን እንደ ፅንስ መጨንገፍ በመሳሰሉ ሁኔታዎች ውድ የሆነን ነገር በማጣት የሚፈጠር ተፈጥሯዊ ስሜት እንደሆነና ሁኔታው ካስከተለው የስሜት መረበሽ ለመላቀቅ የሚቻልበት ሂደት አካል እንደሆነ ይናገራሉ።