የግርጌ ማስታወሻ b በኢየሩሳሌም የነበሩት የመጀመሪያው መቶ ዘመን አይሁዳውያን ክርስቲያኖች ለተወሰነ ጊዜ ያህል በሙሴ ሕግ ውስጥ የተካተቱትን የተለያዩ ሥርዓቶች ያከብሩ ነበር። ይህንን ያደረጉት በሚከተሉት ምክንያቶች የተነሳ ይመስላል። ሕጉን የሰጠው ይሖዋ ነበር። (ሮሜ 7:12, 14) ሕጉ በአይሁድ ሕዝብ መካከል ሥር የሰደደ ልማድ ሆኖ ነበር። (ሥራ 21:20) የአገሪቱ ሕግም የነበረ በመሆኑ ሕጉን መቃወም በክርስትና መልእክት ላይ አላስፈላጊ ተቃውሞ ማስነሳት ይሆን ነበር።