የግርጌ ማስታወሻ
e ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ የሚዋጥ መድኃኒት እንዲወስዱ ማድረግ ተችሏል። አንዳንዶቹ መድኃኒቶች ቆሽት ብዙ ኢንሱሊን እንዲያመነጭ የሚያደርጉ፣ ሌሎቹ በደም ውስጥ ያለው ስኳር መጠን ቶሎ እንዳይጨምር የሚቆጣጠሩ፣ ሌሎቹ ደግሞ ኢንሱሊን ያለመቀበልን ባሕርይ የሚቀንሱ ናቸው። (አብዛኛውን ጊዜ ለዓይነት 1 የስኳር በሽታ የሚዋጥ መድኃኒት አይታዘዝም።) ባሁኑ ጊዜ ኢንሱሊን በአፍ ሊወሰድ አይችልም። ምክንያቱም ወደ ደም ከመግባቱ በፊት የኢንሱሊኑ ፕሮቲን በጨጓራና በአንጀት ውስጥ ይፈርሳል። ኢንሱሊንም ሆነ የሚዋጥ መድኃኒት አካላዊ እንቅስቃሴ የማድረግንና ጤናማ የአመጋገብ ልማድ የመከተልን አስፈላጊነት አያስቀርም።