የግርጌ ማስታወሻ
g ከስኳር በሽተኞች መካከል 90 በመቶ የሚሆኑት ያለባቸው የስኳር በሽታ ዓይነት 2 ነው። ይኸኛው ዓይነት የስኳር በሽታ “ኢንሱሊን የማያስፈልገው” ወይም “ከዕድሜ ጋር የሚመጣ” የስኳር በሽታ ተብሎ ይጠራ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ አጠራር በሽታውን በትክክል አይገልጸውም። ምክንያቱም ዓይነት 2 የስኳር በሽታ ከያዛቸው መካከል 40 በመቶ የሚሆኑት ኢንሱሊን መውሰድ ያስፈልጋቸዋል። ከዚህም በላይ ቁጥራቸው በሚያስደነግጥ ሁኔታ እየተበራከተ የመጣ ገና ጉርምስና ዕድሜ ላይ እንኳን ያልደረሱ ብዙ ልጆች በዓይነት 2 ስኳር በሽታ እየተያዙ ነው።