የግርጌ ማስታወሻ
a በዶክተር ዴኒዝ ሃርሜኒንግ የተዘጋጀው ሞደርን ብለድ ባንኪንግ ኤንድ ትራንስፊውዥን ፕራክቲስስ (ዘመናዊው የደም ባንክና ደም የመስጠት ልማድ) የተሰኘው የመማሪያ መጽሐፍ እንደሚለው “ደም በመውሰዱ ወይም በእርግዝና ምክንያት አሊያም ከሌላ ሰው የተወሰደ አካል ስለተተካለት ቀድሞውንም ሰውነቱ የተቆጣ በሽተኛ . . . ደም ከተሰጠው፣ ከጊዜ በኋላም ቢሆን የቀይ የደም ሴል መፈረካከስ ሊያጋጥመው ይችላል።” እንዲህ ባለው ሁኔታ ሰውነት የተሰጠውን ደም እንዳይቀበል የሚያደርገውን ፀረ እንግዳ አካል (አንቲቦዲ) “ደም ከመሰጠቱ በፊት በሚደረጉት የታወቁ የምርመራ ዘዴዎች ለይቶ ማወቅ አይቻልም።” ዳይሌይስ ኖትስ ኦን ብለድ የተሰኘው ጽሑፍ እንደሚገልጸው የቀይ የደም ሴሎች መፈረካከስ “ከበሽተኛው ደም ጋር የማይስማማ አነስተኛ መጠን ያለው . . . ደም ቢሰጠው እንኳን ሊያጋጥም ይችላል። ኩላሊት ሥራውን ሲያቆም በደም ውስጥ ያለውን ቆሻሻ ማስወገድ ስለማይችል በሽተኛው ቀስ በቀስ ይመረዛል።”