የግርጌ ማስታወሻ
a በቂ እንቅስቃሴ አለማድረግ ለሕይወት አስጊ በሆኑ አንዳንድ በሽታዎች የመያዝ ዕድልን በእጅጉ ይጨምራል። ለምሳሌ የአሜሪካ ልብ ሕመም ማኅበር እንደሚለው በበቂ መጠን አለመንቀሳቀስ “በልብ በሽታ የመያዝን ዕድል በእጥፍ ሲያሳድግ የደም ግፊት መጨመር በሚያስከትለው ችግር የመጠቃት ዕድልን ደግሞ በ30 በመቶ ያሳድጋል። በተጨማሪም በልብ ምትና በደም ዝውውር ችግር የመሞትን እንዲሁም በአንጎል ውስጥ ደም የመፍሰስን አጋጣሚ በእጥፍ ከፍ ያደርጋል።”