የግርጌ ማስታወሻ
a አንዳንዶች በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ላይ የሚገኙት ዓመታት ወራት ብቻ እንደሆኑ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ አርፋክስድ በ35 ዓመቱ ሳላን እንደወለደ ይናገራል። እነዚህን ዓመታት እነርሱ እንደሚሉት 35 ወራት እንደሆኑ አድርገን ከወሰድናቸው አርፋክስድ ሦስት ዓመት ሳይሞላው የልጅ አባት ሆኖ ነበር ማለት ነው። ይህ ደግሞ ፈጽሞ የማይመስል ነገር ነው። በተጨማሪም የዘፍጥረት መጽሐፍ የመጀመሪያዎቹ ምዕራፎች የፀሐይ አቆጣጠር ከጨረቃ አቆጣጠር የተለየ እንደሆነ ይጠቁማሉ።—ዘፍጥረት 1:14-16፤ 7:11