የግርጌ ማስታወሻ
b በአሁኑ ጊዜ ወንዶች ለራሳቸው በተለይ ደግሞ ለውበታቸው ከሚገባው በላይ ትኩረት በመስጠት የሚከተሉት የአኗኗር ዘይቤ (ሜትሮሴክሽዋሊቲ) ግብረ ሰዶም ፈጻሚ በሆኑና ባልሆኑ ወንዶች መካከል ያለው ልዩነት እየደበዘዘ እንዲመጣ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ሜትሮሴክሽዋሊቲ የሚለውን ቃል እንደፈጠሩ የሚነገርላቸው ሰው እንዳሉት ከሆነ ይህ ስያሜ የሚሰጠው ግለሰብ “ግብረ ሰዶም ፈጻሚ ወይም ከተቃራኒ ጾታ ጋር የጾታ ግንኙነት የሚያደርግ አሊያም ከሁለቱም ጾታዎች ጋር ወሲብ የሚፈጽም ሰው ሊሆን ይችላል። ሆኖም ይህ ምንም የሚያመጣው ለውጥ የለም፤ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነቱ ሰው ከራሱ ጋር ፍቅር የያዘው ከመሆኑም በላይ የጾታ ፍላጎቱን የሚያረካለትን ማንኛውንም ዓይነት ወሲባዊ ግንኙነት ይፈጽማል።” ይህ ስያሜ በስፋት እየተሠራበት የመጣው ለምን እንደሆነ አንድ ኢንሳይክሎፒዲያ ሲገልጽ እንዲህ ይላል:- “ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ ሰዎች እንደ ማንኛውም የኅብረተሰብ ክፍል ተደርገው በመታየታቸው እንዲሁም ግብረ ሰዶም እንደ ነውር መታየቱ እየቀረ በመምጣቱና እውነተኛ የወንድነት መገለጫ የሆኑ ነገሮችን በተመለከተ ያለው አመለካከት በመለወጡ ነው።”