የግርጌ ማስታወሻ
b አንድ ልጅ በፆታ ተነወረ የሚባለው አንድ አዋቂ ወንድ (ሴትም ልትሆን ትችላለች) የፆታ ፍላጎቱን ለማርካት ልጆችን መጠቀሚያ ሲያደርጋቸው ነው። ይህ ብዙውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ዝሙት (በግሪክኛ ፖርኒያ) ብሎ የሚጠራውን ድርጊት የሚያጠቃልል ሲሆን ይህም የሌላውን የፆታ ብልት ማሻሸትን፣ የፆታ ግንኙነትንና በአፍ ወይም በፊንጢጣ ወሲብ መፈጸምን የመሳሰሉ ተግባሮችን ይጨምራል። ጡትን ማሻሸት፣ ቀጥተኛ የብልግና ጥያቄዎች ማቅረብ፣ ለልጅ የብልግና ሥዕል ማሳየት፣ ዕርቃናቸውን የሆኑ ወይም የፆታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን በማየት እርካታ ለማግኘት መሞከርና ጨዋነት በጎደለው መልኩ ሰውነትን ማጋለጥ የመሳሰሉት አንዳንድ አስነዋሪ ድርጊቶች፣ መጽሐፍ ቅዱስ ‘የማይረካ ምኞትና ርኵሰት’ ወይም ‘ቅጥ የሌለው ብልግና’ በማለት ካወገዛቸው ድርጊቶች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።—ገላትያ 5:19-21፤ ኤፌሶን 4:19