የግርጌ ማስታወሻ
a ኢየሱስ አቡነ ዘበሰማያት ወይም የጌታ ጸሎት ተብሎ የሚጠራውን የናሙና ጸሎቱን ሲያስተምር “ይህን ጸሎት መጸለይ አለባችሁ” አላለም። ከዚህ ይልቅ “እናንተስ እንዲህ ጸልዩ” ብሏል። (ማቴዎስ 6:9-13 የ1954 ትርጉም) ኢየሱስ ሊያስተምር የፈለገው ቁም ነገር ምን ነበር? ያስተማረው የናሙና ጸሎት እንደሚያሳየው ከቁሳዊ ፍላጎቶቻችን ይበልጥ ቅድሚያ መስጠት ያለብን ለመንፈሳዊ ጉዳዮች ነው።