የግርጌ ማስታወሻ
a ሥነ ፈለክ፣ ከምድራችን ውጪ ባሉ ግዑዛን አካላትና ቁስ አካላት ላይ የሚደረግ ጥናት ነው። ኮስሞሎጂ ደግሞ የሥነ ፈለክ አንዱ ዘርፍ ሲሆን ዘ ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፒዲያ እንደገለጸው “ስለ አጽናፈ ዓለም አወቃቀርና ዕድገት፣ እንዲሁም በውስጡ ስላሉት ኃይሎች የሚያጠና ሳይንስ ነው።” አክሎም “ኮስሞሎጂስቶች አጽናፈ ዓለም የተሠራው እንዴት እንደሆነ፣ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በውስጡ ምን እንደተከናወነና ወደፊት ምን እንደሚከናወን ለማወቅ ጥረት ያደርጋሉ” በማለት ገልጿል።