የግርጌ ማስታወሻ
c የይሖዋ ምሥክሮች የሆኑ ባልና ሚስት ልጃቸው ከመወለዱ በፊት በአካባቢው ያለውን የይሖዋ ምሥክሮች የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴ ሊያማክሩ ይችላሉ። የዚህ ኮሚቴ አባላት ሆስፒታሎችንና ሐኪሞችን ተዘዋውረው በማነጋገር የይሖዋ ምሥክር ለሆኑ ሕሙማን ያለ ደም ስለሚሰጡ ሕክምናዎች መረጃ ይሰጧቸዋል። በተጨማሪም የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴው የሕመምተኛውን እምነት የሚያከብርና ያለ ደም ሕክምና በመስጠት ረገድ ልምድ ያለው ሐኪም በማፈላለግ እገዛ ሊያደርግ ይችላል።