የግርጌ ማስታወሻ
a “ይሖዋ” የሚለውን ስም የፈጠሩት የይሖዋ ምሥክሮች አይደሉም። ለምሳሌ የ1879 ትርጉም ይህን ስም ተጠቅሟል። ከዚህም በላይ እንደ እንግሊዝኛና ጀርመንኛ ያሉ ቋንቋዎች ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት “ጀሆቫ” የሚለውን ስም ይጠቀሙ ነበር። የሚያሳዝነው ግን አንዳንድ ዘመናዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች መለኮታዊውን ስም “አምላክ” እና “ጌታ” እንደሚሉት ባሉ የማዕረግ ስሞች በመተካት ለመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት አክብሮት እንደሌላቸው አሳይተዋል።