የግርጌ ማስታወሻ
a ከዓመታት በፊት ካኒንግሃም (1828) እና ላይክሃርት (1843) የተባሉ አሳሾች የማከዴሚያ ፍሬዎችን የሰበሰቡ ቢሆንም እነሱ የሰበሰቧቸው ናሙናዎች ምንም ዓይነት መግለጫ ሳይጻፍባቸው በመጋዘን እንደተቀመጡ ቀርተዋል። በ1857 የሂል የሥራ ባልደረባ የነበሩት የሜልቦርኑ የሥነ ዕፅዋት ተመራማሪ ፈርዲናንድ ፎን ሙለር፣ ይህን የዛፍ ዝርያ የቅርብ ወዳጃቸው በነበሩት በዶክተር ጆን መካደም ስም ማከዴሚያ ብለው ሰየሙት።