የግርጌ ማስታወሻ a የሰዎች ሕሊና እንደ ሃይማኖታቸውና እንደ መንፈሳዊ ጉልምስናቸው ይለያያል። ትልቅ ቦታ ሊሰጠው የሚገባው ነገር በአምላክ ፊት ንጹሕ ሕሊና ይዞ መገኘት እንዲሁም የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ የሌሎችን ሕሊና የሚጎዳ ነገር አለማድረግ ነው። ሮም 14:10, 12 “ሁላችንም በአምላክ የፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለን” ይላል።