የግርጌ ማስታወሻ a ራእይ 5:11 (የ1954 ትርጉም) በአምላክ ዙፋን ዙሪያ “አእላፋት ጊዜ አእላፋት” መላእክት እንደነበሩ ይገልጻል። እልፍ ሲባል 10,000 ማለት ነው። አንድ እልፍ ሲባዛ አንድ እልፍ (10,000 x 10,000) 100 ሚሊዮን ይሆናል ማለት ነው። ይሁንና ይህ ጥቅስ “አእላፋት ጊዜ አእላፋት” የሚለውን ሐረግ መጠቀሙ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠሩ መንፈሳዊ ፍጥረታት ሊኖሩ እንደሚችሉ ይጠቁማል።