የግርጌ ማስታወሻ
c በቅርብ የተደረጉ ምርምሮች እንደሚያሳዩት ፕሮቲን ለመሥራት የሚያስችል መረጃ ያልያዘው ረጅም አር ኤን ኤ በጣም ውስብስብ ከመሆኑም በላይ ጤናማ ለሆነ እድገት አስፈላጊ ነው። በዚህ አር ኤን ኤ ላይ እክል መኖሩ እንደ ካንሰር፣ ሶራያሲስና አልዛይመር ለመሳሰሉትና ለሌሎች በርካታ በሽታዎች እንደሚያጋልጥ ተመራማሪዎች ደርሰውበታል። ከዚህ በፊት “አሰስ ገሰስ” ተብሎ ይጠራ የነበረው የዲ ኤን ኤ ክፍል የተለያዩ በሽታዎችን መርምሮ ለማወቅና ለማከም የሚያስችል ቁልፍ ሳይሆን አይቀርም!