የግርጌ ማስታወሻ
a ይሁን እንጂ ከቤት ወደቤት እየሄደች በምትሰብክበት ጊዜ ራሷን መሸፈን አያስፈልጋትም ምክንያቱም ምሥራቹን የመስበኩ ኃላፊነት ለሁሉም ክርስቲያኖች የተሰጠ ነው። ነገር ግን ባሏ በተገኘበት የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንድትመራ የሚያስገድድ ሁኔታ ቢያጋጥማት እርሱ ክርስቲያን እንኳን ባይሆን ራስዋ ስለሆነ ራሷን መሸፈን አለባት። በተጨማሪም ቀደም ብሎ የተቋቋመውን የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በምትመራበት ጊዜ የግድ አስፈላጊ ሆኖ አንድ ራሱን የወሰነ የጉባኤ አባል ቢገኝ ራሷን ትሸፈናለች፤ ጸሎቱን ግን እርሱ ማድረግ አለበት።