የግርጌ ማስታወሻ
b ለአንደኛው የዓለም ጦርነት ቄሶች ስለሰጡት ድጋፍ ሰባክያን የጦር መሣሪያ አቀባይ ሆኑ በተባለው በሬይ ኤች አብራምስ (በኒውዮርክ በ1933) በተዘጋጀው መጽሐፍ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷል። መጽሐፉ እንዲህ ሲል ይገልጻል:- “ቄሶች ለጦርነቱ ስሜት የሞላበት መንፈሳዊ ቦታና የሚገፋፋ ኃይል ሰጥተውታል። . . . ጦርነቱ ራሱ የአምላክን መንግሥት በምድር ላይ ለማስፋፋት የሚያገለግል ቅዱስ ጦርነት ነው ተብሎ ተሰበከ። አንድ ሰው ሕይወቱን ለአገሩ መስጠቱ ሕይወቱን ለአምላክና ለመንግሥቱ እንደመስጠት ያህል ተቆጥሮ ነበር። አምላክና አገር ተመሳሳይ ተደርገው ይታዩ ነበር። . . . በዚህ ረገድ ጀርመኖችና ተባባሪዎቻቸው ተመሳሳይ ነበሩ። እያንዳንዱ ወገን አምላክን የራሱ ብቻ እንደሆነ አድርጎ ያምን ነበር። . . . አብዛኞቹ መንፈሳዊ መምህራን በጣም የተጧጧፈ ውጊያ በሚደረግበት ቦታም እንኳ ቢሆን ኢየሱስ ወታደሮቹን ወደ ድል በመምራት ግምባር ቀደም ተዋጊ እንደሆነ አድርገው ለማቅረብ ምንም አልተቸገሩም። . . . በዚህ መንገድ ቤተ ክርስቲያን የጦርነቱ ሂደት መሠረታዊ ክፍል ሆናለች። . . . (የቤተ ክርስቲያን) መሪዎች ራሳቸውን ለጦርነቱ አመቺ አድርገው ለማዘጋጀት ምንም ጊዜ አላጠፉም። ጦርነቱ በታወጀ በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በአሜሪካ የሚገኘው የፌዴራሉ የአብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት የተሟላ ትብብር ለማድረግ ልዩ ልዩ ዕቅዶች ነደፈ። . . . አብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት ከተጠየቁት በጣም አልፈው ሄዱ። ለተመዝጋቢዎቹ ወታደሮች የምልመላ ጣቢያዎች ሆኑ።” — ገጽ 53, 57, 59, 63, 74, 80, 82