የግርጌ ማስታወሻ
b በኢየሱስ እጅ ውስጥ የነበሩት ሰባት ከዋክብት በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ የነበሩ ቅቡዓን የበላይ ተመልካቾችን የሚያመለክቱ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ በምድር በሙሉ በሚገኙት ከ100,000 የሚበልጡ ጉባኤዎች ውስጥ የሚገኙት የበላይ ተመልካቾች የእጅግ ብዙ ሰዎች ክፍል ናቸው። (ራእይ 1:16፤ 7:9) ታዲያ የእነዚህ ደረጃ ምንድን ነው? ሹመታቸውን ያገኙት በተቀባው ታማኝና ልባም ባሪያ አማካኝነት ከመንፈስ ቅዱስ ስለሆነ እነርሱም በኢየሱስ ቀኝ እጅ ቁጥጥር ሥር ያሉ የበታች እረኞች ናቸው። (ኢሳይያስ 61:5, 6፤ ሥራ 20:28) ብቃት ያላቸው ቅቡዓን በማይገኙባቸው ቦታዎች ሁሉ ስለሚያገለግሉ ‘ለሰባቱ ከዋክብት’ ድጋፍ ይሰጣሉ።