የግርጌ ማስታወሻ
a በ19ኛው መቶ ዘመን ይኖሩ የነበሩት የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ጆን ሄንሪ ኒውማን ስለ ክርስትና መሠረተ ትምህርቶች የተዘጋጀ ድርሰት በተባለው መጽሐፋቸው ላይ አብዛኞቹ የሕዝበ ክርስትና መሠረተ ትምህርቶች፣ ክብረ በዓሎችና የአምልኮ ሥርዓቶች ከአረማውያን የመጡ መሆናቸውን ሲያመለክቱ የሚከተለውን ጽፈዋል:- “በቤተ መቅደሶች ማገልገል፣ ቤተ መቅደሶችን በተለዩ ቅዱሳን ስም መሰየም፣ በዛፍ ቅርንጫፎች ማስጌጥ፣ ዕጣን ማጨስ፣ መብራቶችና ጧፎች ማብራት፣ ከበሽታ ሲዳን የስዕለት ቁርባን ማቅረብ፣ ጠበል፣ በዓላትና ዓውደ ዓመታት፣ የቀን መቁጠሪያዎች፣ እርሻዎችን መባረክ፣ የቅዱሳን ሥርዓተ ንግሥ፣ ልብሰ ተክህኖ፣ በጋብቻ ሥርዓት ቀለበት ማድረግ፣ ወደ ምሥራቅ መዞር፣ ከጊዜ በኋላም ሥዕልና ምስል፣ ምናልባትም የቅዳሴ መዝሙሮችና ኪርያላይሶን [ጌታ ሆይ፣ ማረን] የተባለው የምህላ ዝማሬ ከአረማውያን የመጡና ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ አድርጋ የተቀበለቻቸው ናቸው።”
“ሁሉን የሚችለው አምላክ ይሖዋ” ግን እንዲህ ዓይነቱን የጣዖት አምልኮ ከመቀደስ ይልቅ ክርስቲያኖችን “ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ . . . እርኩስንም አትንኩ” በማለት ይመክራል።—2 ቆሮንቶስ 6:14-18