የግርጌ ማስታወሻ
d የሚያስገርመው በ1970ዎቹ በሰሜን ሶርያ ውስጥ የተገኘ የአንድ የጥንት ገዥ ሐውልት አንድ ገዥ ከንጉሥ ያነሰ ሥልጣን ኖሮትም ንጉሥ ተብሎ መጠራቱ እንግዳ ነገር እንዳልሆነ አረጋግጧል። ሐውልቱ የአንድ የጎዛን ገዥ ሐውልት ሲሆን በላዩ በአሦርና በአረማይክ ቋንቋ ተጽፎበታል። በአሦር ቋንቋ የሠፈረው ጽሑፍ ገዥ ብሎ ሲጠራው ተመሳሳይ ሐሳብ የቀረበበት የአረማይክ ጽሑፍ ግን ንጉሥ ብሎታል።9 በመሆኑም ብልጣሶር በኦፊሴላዊ የባቢሎን ጽሑፎች ላይ አልጋ ወራሽ ተብሎ ተጠርቶ ዳንኤል ባሰፈረው የአረማይክ ጽሑፍ ላይ ግን ንጉሥ መባሉ ምንም አያስገርምም።