የግርጌ ማስታወሻ
a የኢሳይያስ መጽሐፍን ጨምሮ የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች መጻሕፍት ከመጀመሪያው መቶ ዘመን እዘአ ብዙ ቀደም ብሎ ተጽፈው ያለቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ማስረጃ አለ። ታሪክ ጸሐፊው ጆሴፈስ (መጀመሪያው መቶ ዘመን እዘአ) የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ከእርሱ ዘመን ብዙ ቀደም ብለው ተጽፈው ያለቁ መሆናቸውን አመልክቷል።8 በተጨማሪም የግሪክ ሴፕቱጀንት የተባለው የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች የግሪክኛ ትርጉም በሦስተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ ተጀምሮ በሁለተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ ተጠናቅቆ ነበር።