የግርጌ ማስታወሻ
d በተቃራኒው ግን ሐዋርያው ጳውሎስ በዕብራውያን ምዕራፍ 11 ላይ በመንፈስ አነሳሽነት ያሰፈረው የታመኑ ወንዶችና ሴቶች ዝርዝር በዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱትን ክስተቶች በተዘዋዋሪ መንገድ የሚጠቅስ ይመስላል። (ዳንኤል 6:16-24፤ ዕብራውያን 11:32, 33) ሆኖም ሐዋርያው የጠቀሰውም ዝርዝር ቢሆን ሁሉንም የሚያቅፍ አይደለም። እንደ ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ እና ሕዝቅኤል የመሰሉ በዚህ ዝርዝር ውስጥ በስም ያልተጠቀሱ ብዙ ሰዎች አሉ። ይሁን እንጂ እነዚህ ሰዎች በሕይወት አልነበሩም ማለት አይደለም።