የግርጌ ማስታወሻ
c ምሁራን “ለማንም አልራራም” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጡ አገላለጽ ለመተርጎም “እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ሐረግ” እንደሆነ ይናገራሉ። “አልራራም” የሚለው ቃል የገባው ይሖዋ ባቢሎንን እንዳያጠፋ ማንም ሰው ቢለምነው የማይሰማ መሆኑን ለማመልከት ነው። የአይሁድ የኅትመት ማኅበር ያዘጋጀው ትርጉም ይህን ሐረግ “ማንም ሰው ጣልቃ ገብቶ እንዲማልድ . . . አልሻም” ሲል ተርጉሞታል።