የግርጌ ማስታወሻ c ፈሪሳውያን ሕግን ያልተማረው ተራው ሕዝብ “የተረገመ ነው” የሚል አመለካከት ነበራቸው። (ዮሐንስ 7:49) ማንም ሰው እንዲህ ያሉትን ሰዎች ማስተማር ወይም ከእነዚህ ሰዎች ጋር መነገድ፣ መብላት ወይም መጸለይ የለበትም ይሉ ነበር። አንድ ሰው ሴት ልጁን እንዲህ ላለ ሰው ቢድር ለአውሬ እንደሰጣት ተደርጎ ይቆጠር ነበር። ፈሪሳውያን እነዚህ ተራ ሰዎች ትንሣኤ የማግኘት ተስፋ እንኳ የላቸውም የሚል እምነት ነበራቸው።