የግርጌ ማስታወሻ
a የጥንት ገልባጮች (ሶፌሪም) ይህን ጥቅስ ሲገለብጡ ወደ ታች ያጎነበሰው ይሖዋ ሳይሆን ኤርምያስ እንደሆነ አድርገው ጽፈዋል። በዚህ መንገድ የጻፉት አምላክ እንዲህ ያለውን ትሕትና የሚጠይቅ ድርጊት ይፈጽማል ብለው መጻፍ ተገቢ እንደሆነ ስላልተሰማቸው መሆን አለበት። በዚህም የተነሳ ይህ ግሩም ጥቅስ በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ላይ በትክክል ሳይተረጎም ቀርቷል። ይሁን እንጂ ዘ ኒው ኢንግሊሽ ባይብል ኤርምያስ “አስበኝ፣ አቤቱ አስበኝ፣ ወደ እኔም ጎንበስ በል” ሲል አምላክን እንደተማጸነ በመግለጽ ይህን ጥቅስ በትክክል ተርጉሞታል።