የግርጌ ማስታወሻ
a የረቢዎች ሕግ ማንም ሰው የሥጋ ደዌ በሽተኞችን ሁለት ሜትር ገደማ መራቅ እንዳለበት ያዝዛል። ነፋስ የሚነፍስ ከሆነ ደግሞ ሕመምተኛው ቢያንስ 45 ሜትር ገደማ መራቅ ነበረበት። ሚድራሽ ራባ የተባለው የአይሁዶች መጽሐፍ አንድ ረቢ ከሥጋ ደዌ በሽተኞች ይሸሸግ እንደነበረ፣ ሌላው ረቢ ደግሞ እንዳይጠጉት ሲል ድንጋይ ይወረውርባቸው እንደነበር ይገልጻል። የሥጋ ደዌ በሽተኞች ሕዝቡ በጣም ያገልላቸውና ይጸየፋቸው የነበረ በመሆኑ ስሜታቸው ይጎዳ ነበር።