የግርጌ ማስታወሻ
d በባቢሎን ላይ የደረሰው ጥፋት ፍጻሜያቸውን ካገኙት የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች መካከል አንዱ ምሳሌ ብቻ ነው። ሌሎቹ ምሳሌዎች በጢሮስና በነነዌ ላይ የደረሰውን ጥፋት ያካትታሉ። (ሕዝቅኤል 26:1-5፤ ሶፎንያስ 2:13-15) በተጨማሪም የዳንኤል ትንቢት ከባቢሎን በኋላ የዓለም ኃያል መንግሥት ሆነው ተራ በተራ የሚነሱ ብሔራትን ተንብዮ ነበር። እነዚህም ሜዶ ፋርስንና ግሪክን ያጠቃልላሉ። (ዳንኤል 8:5-7, 20-22) በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተፈጸሙትን ስለ መሲሑ የተነገሩ በርካታ ትንቢቶች በተመለከተ ማብራሪያ ለማግኘት ከገጽ 199-201 ላይ ያለውን ተጨማሪ ክፍል ተመልከት።