የግርጌ ማስታወሻ
a መጽሐፍ ቅዱስ ሕሊናችን የማይወቅሰን መሆኑ ብቻ ሁልጊዜ በቂ እንደማይሆን ይጠቁማል። ለምሳሌ ጳውሎስ “እኔ ሕሊናዬን የሚወቅሰኝ ምንም ነገር የለም። ሆኖም ይህ ጻድቅ መሆኔን ያረጋግጣል ማለት አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ እኔን የሚመረምረኝ ይሖዋ ነው” ሲል ተናግሯል። (1 ቆሮንቶስ 4:4) ጳውሎስ በአንድ ወቅት ያደርግ እንደነበረው ክርስቲያኖችን የሚያሳድዱ ሰዎች እንኳ ድርጊታቸውን አምላክ የሚቀበለው ስለሚመስላቸው ንጹሕ ሕሊና ሊኖራቸው ይችላል። ሕሊናችን በራሳችንም ሆነ በአምላክ ዓይን ንጹሕ መሆኑ አስፈላጊ ነው።—የሐዋርያት ሥራ 23:1፤ 2 ጢሞቴዎስ 1:3