የግርጌ ማስታወሻ
c በ1 ሳሙኤል 23:17 ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ዮናታን ዳዊትን ለማበረታታት አምስት ነገሮች ተናግሯል:- (1) ዳዊት እንዳይፈራ መከረው። (2) ሳኦል የሚያደርገው ጥረት እንደማይሳካ አረጋገጠለት። (3) አምላክ ቃል እንደገባለት ንግሥናውን ማግኘቱ እንደማይቀር ነገረው። (4) ለዳዊት ታማኝ ሆኖ እንደሚቀጥል ቃል ገባለት። (5) ሳኦልም ዮናታን ለዳዊት ታማኝ መሆኑን እንደሚያውቅ ነገረው።