የግርጌ ማስታወሻ
a አንድ ምሁር እንደገለጹት በዘመኑ በነበረው የቄሳር ሕግ መሠረት “አዲስ ንጉሥ ወይም መንግሥት እንደሚመጣ በተለይም በወቅቱ ያለውን ንጉሠ ነገሥት እንደሚተካ ወይም በእሱ ላይ እንደሚፈርድ” መተንበይ የተከለከለ ነው። ተቃዋሚዎች የጳውሎስን መልእክት በማጣመም ሳይሆን አይቀርም ይህን ሕግ የሚጥስ ነገር እንዳደረገ በመግለጽ ወንጅለውታል። “ቄሳሮችና የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።